1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአሸባብ ከፍተኛ መሪ ሶማሊያ ውስጥ ተያዘ

ቅዳሜ፣ ታኅሣሥ 18 2007

የአልሸባብ ከፍተኛ መሪ እንደሆነ የሚነገርለት ዛካሪያ ኢስማይል አህመድ ሔርሲ ሶማሊያ ውስጥ መማረኩን ዛሬ አንድ የሶማሊያ የደኅንነት ሹም አስታወቁ።

https://p.dw.com/p/1EAet
Nairobi Kenia Terroranschlag Al-Shabaab Einkaufszentrum Westgate Mall
ምስል SIMON MAINA/AFP/Getty Images

ዘካሪያን ይዞ ላቀረበ አለያም ያለበትን ለጠቆመ 3 ሚሊዮን ዶላር ወሮታ እንደሚከፈል ቀደም ሲል ተጠቅሶ ነበር። ከአልሸባብ ከፍተኛ አመራር አንዱ የሆነው ዛካሪያ ኢስማይል ሶማሊያ ጌዶ ውስጥ መያዙን ይፋ ያደረጉት የደኅንነት ሹም ለጋዜጠኞች መግለጫ ለመስጠት ፈቃድ ስለሌላቸው ስማቸው እንዳይጠቀስ መፈለጋቸውም ተዘግቧል። ባለሥልጣኑ ዛካሪያ ኢስማይል ሊያዝ የቻለው በዩናይትድ ስቴትስ የጦር አውሮፕላን ጥቃት ከተገደለው የአሸባብ ከፍተኛ መሪ አህመድ ጉዳኔ ታማኞች ጋር በመቃረኑ ሳይሆን እንዳልቀረ ግምታቸውን ገልጠዋል። የአሸባብ ቡድን እስካሁን በዚህ ላይ ምላሽ አልሰጠም። የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ከዛሬ 2 ዓመት በፊት ዛካሪያ ኢስማይልን ጨምሮ 8 የአልሸባብ ባለሥልጣናት የሚገኙበትን ለጠቆመ 33 ሚሊዮን ዶላር ለመስጠት ቃል ገብቶ ነበር። አልሸባብ የተሰኘው የሶማሊያ ታጣቂ ቡድን መዲና ሞቃዲሾ ውስጥ የነበረውን ይዞታ ከማጣቱም ባሻገር የሶማሊያ እና የኬንያ ስጋት በመሆን ተወስኗል ሲል አሶሺየትድ ፕሬስ ዘግቧል።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ልደት አበበ