የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መራዘም
ሐሙስ፣ መጋቢት 21 2009ማስታወቂያ
አቶ ሲራጅ ፈጌሳን አዋጁ እንዲራዘም የተፈለገው ባለፉት ስድስት ወራት በመላ ሀገሪቱ የተገኘውን አንጻራዊ ሰላም እና መረጋጋት ወደ ማይቀለበስበት ደረጃ ለማድረስ ነው ማለታቸው ተዘግቧል ።በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ለአንድ ዓመት ገደማ ፀረ መንግሥት ተቃውሞ ከተካሄደ በኋላ ነበር ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ባለፈው መስከረም 29 ፣ 2009 ዓም የአስቸኳዩን ጊዜ ያወጁት። በመብት ተሟጋች ድርጅቶች መሰረት፣ በነዚህ ተቃውሞ ወቅት የፀጥታ ኃይላት በወሰዱት የኃይል እርምጃ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገድለዋል። የተቃዋሚ ፓርቲዎች መንግሥት አዋጁን በተለይ፣ በገጠሩ አካባቢ ያሉትን አባሎቻቸውን እና ስራቸውን ለማፈን እየተጠቀመበት ነው ሲሉ ወቅሰዋል። አዋጁ መራዘሙ ሀገሪቱ የምትገኝበትን አደገኛ ሁኔታ እንደሚያሳይ ዶይቸ ቬለ ያነጋገራቸው ተቃዋሚው የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀ መንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ ለዶይቸ ቬለ ገልጸዋል።
አርያም ተክሌ
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ