1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአምነስቲ እና የጋዜጠኛ አስተያየት

ቅዳሜ፣ የካቲት 3 2010

ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል የኢትዮጵያ መንግሥት በእስር ላይ የሚገኙ 746 ታራሚዎች እና ተጠርጣሪዎች ለመልቀቅ መወሰኑን« ግሩም ዜና » ሲል አወደሰ። ድርጅቱ «ደፋሩ ጋዜጠኛ ከእንግዲህ አንዲት ቀን እንኳ በእስር ሊያሳልፍ አይገባም ሲል ገልፆአል።

https://p.dw.com/p/2sQXb
Logo von Amnesty International

«እስረኞችን ከመፍታቱ ጎን የፍትህ ሥርዓቱን አስተማማኝ ሊሆን ይገባል።»

 

ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተከራካሪ ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል የኢትዮጵያ መንግሥት በእስር ላይ የሚገኙ 746 ታራሚዎች እና ተጠርጣሪዎች ለመልቀቅ መወሰኑን« ግሩም ዜና » ሲል አወደሰ። ድርጅቱ ባወጣዉ መግለጫ «ደፋሩ ጋዜጠኛ ስራዉን ስለሰራ ብቻ ከሰባት ዓመታት እስር በኋላ ወደ በቅርቡ ነፃ ይወጣል፤ ከእንግዲህ አንዲት ቀን እንኳ በእስር ሊያሳልፍ አይገባም ሲል ገልፆአል። የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የአፍሪቃ ቀንድ ተመራማሪ አቶ ፍስሃ ተክሌን እና ጋዜጠኛ አናኒያ ሶሪን አስተያየታቸዉን ጠይቀን ዘገባ አዘጋጅተናል።

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና አንዱዓለም አራጌን ጨምሮ በእስር ላይ የሚገኙ 746 ታራሚዎች እና ተጠርጣሪዎች እንደሚለቀቁ የመንግሥት መገናኛ ብዙሀን ይፋ ካደረጉ በኋላ በሐገር ዉስጥም ሆነ ከሐገርዉ ዉጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን በተለያዩ ዘዴዎች ደስታቸዉን ገልፀዋል። የተለያዩ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅቶችም ርምጃዉን በማወደስ መግለጫ አዉጥተዋል። መቀመጫዉን ናይሮቢ ኬንያ ያደረገዉ አምነስቲ ኢንተርናሽናል የአፍሪቃ ቀንድ ተመራማሪ አቶ ፍስሃ ተክሌ ከኢትዮጵያ የተሰማዉ ዜና አስደሳች ነዉ፤ ሁሉም የሕሊና እስረኞች እንዲፈቱም እንጠይቃልን ሲሉ ገልፀዋል። 

የአምነስቲ የአፍሪቃ ቀንድ ተመራማሪ ምህረት ተደረገላቸዉ የተባሉት እስረኞች መፈታታቸዉ አንድ ነገር ሆኖ ተፈችዎቹ በቀጣይ ሥራቸዉን እንዲተገብሩ እና መሠረት የሌለዉ ክስ ተጥሎባቸዉ እንዳይታሰሩ ዋስትና የሚሰጣቸዉ ርምጃዎች መኖር አለባቸዉ ብለዋል።  

የቀድሞ የአንድነት ለፍትህ እና ለዴሞክራሲ ፓርቲ አባል እና ጋዜጠኛ አናንያ ሶሪ በበኩሉ ዜናዉ አስደሳች ቢሆንም ተቃራኒ የሆኑ መረጃዎች ሊጠሩ ይገባል ሲል ተናግሮአል።

የህሊና እስረኞችን ከመፍታቱ ጋር ጎን ለጎን የፍትህ ሥርዓቱን በአስተማማኝ ቦታ ላይ ማስቀመጥ ያስፈልጋል ያለዉ ጋዜጠኛ አናንያ ሶሪ በመቀጠል

 

አዜብ ታደሰ

ኂሩት መለሰ