1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአሜሪካ ምርጫና ተቃዉሞ

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 5 2008

እራሳቸዉን የዴሞክራሲ ንቅናቄ ብለዉ የሚጠሩት ወገኖች የአሜሪካ ምርጫ እና ፖለቲካ በቱጃር ኩባንያ፤ ድርጅቶች፤ ተቋማትና ግለሠቦች መነዳቱ እንዲቆም ጠይቀዋል።

https://p.dw.com/p/1IUkD
ምስል Getty Images/M. Wilson

[No title]

የዩናይትድ ስቴትስ ተቀናቃኝ ፖለቲከኞች የሚያደርጉት የምረጡኝ ዘመቻ የአብዛኛዉን አሜሪካዊ ትኩረት በሳበበት ባሁኑ ወቅት የሐገሪቱን የምርጫ ሒደትና የሐብታም ድርጅቶችን ጣልቃገብነት የሚቃወሙ አሜሪካዉያን ላደባባይ ሠልፍ እየታደሙ ነዉ።እራሳቸዉን የዴሞክራሲ ንቅናቄ ብለዉ የሚጠሩት ወገኖች የአሜሪካ ምርጫ እና ፖለቲካ በቱጃር ኩባንያ፤ ድርጅቶች፤ ተቋማትና ግለሠቦች መነዳቱ እንዲቆም ጠይቀዋል።በቅርቡ ርዕሠ-ከተማ ዋሽንግተን ዲሲ አደባባይ የወጡ ተቃዋሚዎች ከፀጥታ አስከባሪዎች ጋር ተጋጭተዉም ነበር።የዋሽግተን ዲሲዉ ወኪላችን መክብብ ሸዋ የላከልን ዘገባ አለ።

መክብብ ሸዋ

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሠ