የአሜሪካን ተጨማሪ እርዳታ
ዓርብ፣ ነሐሴ 6 2003ማስታወቂያ
የአሜሪካን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሂለሪ ክሊንተን ትናንት በሰጡት መግለጫ ሃገራቸው በድርቅና ረሃብ ለተጎዱት የአፍሪቃ ቀንድ አገራት የ 17 ሚሊዮን ዶላር ተጨማሪ እርዳታ እንደምትሰጥ አስታውቀዋል ። ከዚህ እርዳታ ከሁለት ሶስተኛ በላይ የሚሆነውንም ለሶማሊያ የሚለገስ ነው ። ክሊንተን በዚሁ መግለጫቸው ተመሳሳይ የረሃብ አደጋዎችን እንዳይደርሱ ሁሉን አቀፍ ዛላቂ እርምጃዎችን መውሰድ እንደሚጋባም አሳስበዋል ። ክሊንተን እንዳሉት የረሐብ አደጋን ለመከላከል የዓለም ማሕበረሰብ በግብርናና በተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት ላይ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ ይገባዋል ። አበበ ፈለቀ ከዋሽንግተን ዲሲ ዝርዝር ዘገባ አዘጋጅቷል ።
አበበ ፈለቀ
ሂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሰ