1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአማሮ ፣ የቡርጂ እና የሰገን አካባቢዎች በልዩ ወታደራዊ እዝ እንዲመሩ መወሰኑ 

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 30 2011

ቢሮው እንዳስታወቀው አካባቢው በልዩ የወታደራዊ ዕዝ  እንዲመራ የወሰነው የታጠቁ ኃይሎች በሚሰነዝሩት  ጥቃት በነዋሪዎች ላይ እየደረስ የሚገኘው ሰብአዊ ቀውስ እየተባባሰ በመምጣቱ ነው ።የአማሮ እና የቡርጂ ባለስልጣናት በበኩላቸው አሁን የተወሰደው እርምጃ የዘገየ ቢሆንም ገለልተኛ ኃይል መግባቱ የአካባቢውን ሰላም ለመመለስ እንደሚያስችል ገልፀዋል።

https://p.dw.com/p/3IBZb
20.06.2013 DW Online Karten Basis Aethiopien spanisch

የአማሮ ፣ የቡርጂ እና የሰገን አካባቢዎች በልዩ ወታደራዊ እዝ እንዲመሩ መወሰኑ 

የደቡብ ክልልን ከጉጂ ዞን የሚያዋስኑት የአማሮ ፣ የቡርጂ እና የሰገን አካባቢዎች ከዛሬ  ጀምሮ በፌደራል የመከላከያ ሠራዊት በሚመራ ልዩ ወታደራዊ ዕዝ ( ኮማንድ ፖስት ) ስር አንዲመሩ መወሰኑን የክልሉ ሠላምና ፀጥታ ቢሮ አስታወቀ። ቢሮው እንዳስታወቀው አካባቢው በልዩ የወታደራዊ ዕዝ  እንዲመራ የወሰነው የታጠቁ ኃይሎች በሚሰነዝሩት  ጥቃት በነዋሪዎች ላይ እየደረስ የሚገኘው ሰብአዊ ቀውስ እየተባባሰ በመምጣቱ ነው ።የአማሮ እና የቡርጂ ባለስልጣናት በበኩላቸው አሁን የተወሰደው እርምጃ የዘገየ ቢሆንም ገለልተኛ ኃይል መግባቱ የአካባቢውን ሰላም ለመመለስ እንደሚያስችል ገልፀዋል። የሀዋሳው ዘጋቢያችን ሸዋንግዛው ወጋየሁ ተጨማሪ ዘገባ ልኮልናል። 


ሸዋንግዛው ወጋየሁ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ