የአማራ እና ኦሮሚያ የፀጥታ ኃላፊዎች መግለጫ
ሐሙስ፣ መጋቢት 19 2011ማስታወቂያ
በአማራና አሮሚያ አዋሳኝ አንዳንድ አካባቢዎች፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በአዲስ አበባ የባለቤትነት ጉዳይ ላይ የሁለቱንም ህዝቦች ሰላምና አንድነት የሚፈታተኑ ሁኔታዎች ይታያሉ፡፡ በየጊዜው የሚነሱ የሰላም ጠንቆችን በዘላቂነት ለመፍታት ሚያስችል ውይይት በሁለቱ የፀጥታ ቢሮ ከፍተኛ ኃላፊዎች መካከል ትናንትና በባህር ዳር ከተማ ተካሂዷል፡፡ የውይይቱን አስፈላጊነትና የተደረሰበትን ድምዳሜ አስመልክቶ ዛሬ የአማራና ኦሮሚያ ክልሎች ከፍተኛ የፀጥታ ኃላፊዎች ለመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ከስፍራው ዘሃቢያችን ዓለምነው መኮንን ዝርዝሩን ልኮልናል።
ዓለምነው መኮንን
ሸዋዬ ለገሠ
ኂሩት መለሰ