ኤኮኖሚ
የኖትር ዳም ቃጠሎ
ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 8 2011ማስታወቂያ
ትናንት በእሳት የጋየዉን የፓሪሱን የኖትር ዳም ካቲድራልን መልሶ ለመጠገን የሐገራት መሪዎች፣ድርጅቶችና ኩባንዮች የሞራል፤የሙያና የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ እየተረባረቡ ነዉ።የጀርመኑ ፕሬዝደንት ፍራንክ ቫልተር-ሻትይን ማየር «የአዉሮጳ መለያ» ያሉትን ካቲድራል ለመጠገን የጀርመንና የመለዉ አዉሮጳ ሕዝብ እርዳታ እንዲሰጥ ጠይቀዋል።በጥንታዊ ሥነ-ሕንፃ ጥበብ የታወቁት የግሪክና የቼክ መንግሥታት ባለሙያዎች ለመላክ ዝግጁ መሆናቸዉን አስታዉቀዋል።የፈረንሳይ ቱጃሮች ቤርናር አርኖ እና ፍራንሷ ፒኖ 300 ሚሊዮን ዩሮ፣ የፈረንሳዩ የነዳጅ ኩባንያ ቶታል 100 ሚሊዮን፣የፈረንሳዩ የመዋቢያዎች አምራች ሎ ርየል 100 ሚሊዮን ዩሮ ለመስጠት ቃል ገብተዋል።ሌሎችም እርዳታ መስጠታቸዉን እንደቀጠሉ ነዉ።
ሐይማኖት ጥሩነሕ
ነጋሽ መሐመድ
ማንተጋፍቶት ስለሺ