1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቤንዚን ማደያ እጥረት የነዳጅ እጥረቱን አባብሶታል

ዓርብ፣ ጥር 5 2009

በያዝነዉ ሳምንት መግብያ የኢትዮጵያ ንግድ ሚኒስቴር በነዳጅ ምርቶች ችርቻሮ ላይ የዋጋ ጭማሪ ማድረጉን ይፋ ካደረገ በኋላ በተለይ የአዲስ አበባ ከተማ ላይ ብዙም ለዉጥ አለመታየቱን አንዳንድ ነዋሪዎች ገለፁ።

https://p.dw.com/p/2Vmos
Mosambik Ponta do Ouro Tankstelle
ምስል imago/Anka Agency International

Ber. A.A. (Benzinpreis schießt in die Höhe) - MP3-Stereo


የዋጋ ጭማሪዉ  በአንድ  ሊትር ቤንዚን ላይ አንድ ብር ከሰላሳ አንድ ሳንቲም ፤ ናፍጣ ላይ ደግሞ አንድ ብር ከዜሮ ሁለት ሳንቲም መጨመሩን ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ በበኩላቸዉ በሀገሪቱ በሚገኙ ትልልቅ ከተሞች በተለይም ደግሞ በአዲስ አበባ በቂ የነዳጅ ማደያ ባለመኖሩ ለነዋሪዎች ምርቱን ለማዳረስ የሚደረገዉን ሥራ እንደሚያጓትተዉ ገልፀዋል።  በየከተማዉ የሚገኘዉ የቤንዚን ማድያ የከተሞችን እድገትና ከፍተኛ ቁጥር ተሽከርካሪዎችን ያላጤነ ነዉም ተብሎአል። ዝርዝሩን የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ልኮልናል።  


ጌታቸዉ ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ