1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኅብረተሰብ ፀጥታ እና ደህንነት ስጋት በባሕር ዳር

ማክሰኞ፣ ግንቦት 20 2011

መታፈን እና ገንዘብ መዘረፍ የከተማዋ ነዋሪዎች በየጊዜው የሚያሰሙት አቤቱታ ነው፡፡ ከሰሞኑም በድርጊቱ የተጠረጠሩ በቁጥጥር ሥር የመዋላቸው ጉዳይ መሰማቱን ከባሕር ዳር ወኪላችን ዓለምነው መኮንን ዘግቧል።

https://p.dw.com/p/3JLoX
Äthiopien | Diskussion über Bürger Sicherheitslage
ምስል DW/A. Mekonnen

በባሕር ዳር ከተማ ዝርፊያ፣ ወከባና ስርቆት ነዋሪዎችን እያማረረ ነው፡፡ ሴቶች የእጅ ስልካቸውን እንደሚነጠቁ ፣ ጌጣግጥ አድርገውም ከተማ መውጣት እንደተቸገሩ ይናገራሉ፡፡ ስለሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎችም እንዲሁ መታፈን እና ገንዘብ መዘረፍ የከተማዋ ነዋሪዎች በየጊዜው የሚያሰሙት አቤቱታ ነው፡፡ ከሰሞኑም በድርጊቱ የተጠረጠሩ በቁጥጥር ሥር የመዋላቸው ጉዳይ መሰማቱን ከባሕር ዳር ዘጋቢያችን ዓለምነው መኮንን የላከልን ዘገባ ያስረዳል።
ዓለምነው መኮንን

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ