1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የትግራይ ክልል የምርጫ ዝግጅት

ሰኞ፣ ሰኔ 22 2012

አዲስ የሚቋቋመው የምርጫ ኮምሽን የትግራይን ምርጫ ይመራል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተነግሯል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በትግራይ የሚደረግ ምርጫን የመፍቀድም ሆነ የመከልከል መብት የለውም ያለው የትግራይ ምክር ቤት ከሚሽኑን ለማቋቋምና ምርጫን ለማስፈጸም ያስችላሉ የተባሉ ረቂቅ አዋጆችን ዝግጅትም እያጠናቀቀ መሆኑን ምንጮች ለዶቼቬለ ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/3eWJm
Äthiopien Stadtansicht Mekele
ምስል DW/M. Hailessilasie

የትግራይ ክልል የምርጫ ዝግጅት

ምርጫ ለማካሄድ ያቀረበው ጥያቄ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ውድቅ የተደረገበት የትግራይ ክልላዊ መንግሥት የራሱን የምርጫ ኮሚሽን ሊያቋቁም መሆኑ ተሰምቷል።አዲስ የሚቋቋመው የምርጫ ኮምሽንም የትግራይን ምርጫ ይመራል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተነግሯል።የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በትግራይ የሚደረግ ምርጫን የመፍቀድም ሆነ የመከልከል መብት የለውም ያለው የትግራይ ምክር ቤት ከሚሽኑን ለማቋቋምና ምርጫን ለማስፈጸም ያስችላሉ የተባሉ ረቂቅ አዋጆችን ዝግጅትም እያጠናቀቀ መሆኑን ምንጮች ለዶቼቬለ ተናግረዋል።ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ ከመቀሌ ዝርዝር ዘገባ አለው።
ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ 
ኂሩት መለሰ
እሸቴ በቀለ