1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል ዓመታዊ ሠንጠረዥ

ሐሙስ፣ ኅዳር 27 2005

በየሀገሩ ሙስና የሚገኝበትን ደረጃ የሚገመግመው መንበሩን በርሊን ያደረገው ድርጅት «ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል» ዓመታዊ ዘገባውን አቀረበ። ድርጅቱ ከ 170 የሚበልጡ ሀገራት የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች እና ሌሎች ተቋማትን አሰራርን

https://p.dw.com/p/16wsi
***Das Logo darf nur in Zusammenhang mit einer Berichterstattung über die Institution verwendet werden *** Transparency International, kurz TI, ist eine weltweit agierende nichtstaatliche Organisation mit Sitz in Berlin, die sich in der nationalen und internationalen volks- und betriebswirtschaftlichen Korruptionsbekämpfung engagiert. Quelle;: Wikipedia

መርምሮ የሚገኙበትን የሙስና ደረጃ በዝርዝር አስቀምጧል። ምርመራው ከተመለከታቸው ሀገራት መካከል ሁለት ሦስተኛዎቹ ትልቅ ችግር እንዳለባቸው አንድም ሀገር ሙሉውን ውጤት ሙስና ነፃ ባትሆንም በተለይ በግሪክ ያለው ሁኔታ አሰደንጋጭ መሆኑን ድርጅቱ ገልጾዋል።
በመንግሥት ተቋማት ውስጥ በሚሰሩት ዘንድ ጉቦኝነት፡ በዘመድ አዝማድ መጠቃቀም እና ለጥቅም መገዛት ምን ያህል መስፋፋቱን የሚያሳይ አስተማማኝ መለኪያ መሆኑ የሚነገርለት የትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል የዘንድሮ ዘገባ በሶማልያ፡ ሰሜን ኮርያ እና በአፍጋኒስታን የመንግሥት ተቋማት ውስጥ ሙስና እጅግ የተስፋፋ መሆኑን አሳይቶዋል። እነዚሁ በመዘርዝሩ አንድ መቶ ሰባ አራተኛውን ቦታ የያዙት ሦስት ሀገራት አምና ይገኙበት ከነበረው ደረጃ አንዳችም መሻሻል አለማድረጋቸውን በሰንጠረዡ ተቀምጦዋል። ድርጅቱ ከንዑሱ እስከ ግዙፉ የሙስና ደረጃ ከሰጠው ዜሮ እስከ አንድ መቶ ነጥብ ሦስቱ ሀገራት ስምንት ብቻ ነው ያገኙት። የመዘርዝሩን ቀዳሚ ቦታዎች የያዙት ዘጠና ነጥብ ያገኙት እና አምናም በአርአያነት የተጠቀሱት ዴንማርክ፡ ፊንላንድ እና ኒውዚላንድ ናቸው። ዩኤስ አሜሪካ 19ኛ፤ ቻይና 80 ኛ ሲሆኑ፡ ጀርመን አንድ ደረጃ አሻሽላ 13 ኛውን ቦታ ስትይዝ፡ ባጠቃላይ ብዙዎቹ የአውሮጳ ሀገራት፡ በተለይም በዩሮ ተጠቃሚ የሆኑት ሀገራት ደህና ውጤት ማስመዝገባቸውን የትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል መዘርዝሩ አሳይቶዋል። የፊናንስ ቀውስ በገጠማት ግሪክ ሙስናው እጅግ ተስፋፍቶ ሀገሪቱ በመዘርዝሩ የ 94 ኛ ቦታን ይዛለች። አምና 80 ኛ ነበረች።
ከአፍሪቃ ቦትስዋ፡ ኬፕ ቬርዴ፡ ሞሪሽየስና ሴይሼልስ ደህና ቦታ አግኝተዋል። ከሰሃራ በስተደቡብ ባሉት አፍሪቃውያት ሀገራት ሙስና ትልቅ ችግር መደቀኑን ድርጅቱ ገልጾዋል። በመዘርዝሩ ከታዩት 176 ሀገራት መካከል በአፍሪቃ ቀንድ የሚገኙት ኢትዮጵያ 113 ኛ፡ ኤርትራ ደግሞ 150 ፡ ሱዳን ደግሞ 173 ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ። ይሁንና፡ በኢትዮጵያ ያለውን የሙስናው ደረጃ ስናይ መጥፎ የሚባል እንዳልሆነ የአፍሪቃ ክፍል ዳይሬክተር ሻንታል ኡሚማና ለዶይቸ ቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ አስታውቀዋል።
« ኢትዮጵያ 33 ነጥቦችን አግኝታለች። ይህ ከሰሀራ በስተደቡብ ላሉት ሀገራት አማካይ የሚባል ነጥብ ነው። ይህ ገሀድም የሚያሳየው ሁኔታዎች እንደተሻሻሉ ነው። »
ድርጅቱ የሙስናን ደረጃ በመመርመሩ ስራው ላይ ትብብር በሀገሪቱ ካሉ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ትብብር ማግኘቱን ወይዘሮ ሻንታል ቢገልጹም፡ ሲቭል ማህበራት ባረፈባቸው ገደብ የተነሳ ስራቸውን እንደልብ ማከናወን እንደማይችሉና ጉዳዩ አሁንም አነጋጋሪ እንደሆነ አስታውቀዋል።
«እንደምታውቁት፡ ለመብት የሚሟገቱ ብዙ ሲቭል ማህበራት ይህንኑ ስራቸውን በሚያከናውኑበት ሂደት ላይ ገደብ አርፎባቸዋል። ለስራቸው የሚያስፈልገውንና በሀገር ውስጥ ማሰባሰብ ያልቻሉትን ወጪ ከውጭ ለጋሾች ለማግኘት የሚያደርጉት ጥረታቸው ገደብ አርፎበታል። ለነገሩ ፀረ ሙስናው ትግል የፖለቲካ ጉዳይ ሳይሆን፣ የልማት ስራ ነው። ምክንያቱም ፣ ሙስና ልማትን ያሰናክላል። ግን፣ የድርጅታችን የኢትዮጵያ ምዕራፍ አሁንም ቢሆን በሙስና አንፃር የሕዝቡን ግንዛቤ ከፍ ለማድረግ የጀመረውን ስራ እና አጋጣሚው በፈቀደለትም ቁጥር ምርመራውን አለማቋረጡን ነው ባጭሩ ለመግለጽ የምፈልገው። »
በተለይ ሙስና የተስፋፋባቸው ሀገራት መንግሥታት ለፀረ ሙስናው ትግል ቀዳሚ ቦታ እንዲሰጡ ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል አሳስቦዋል።

***Für mögliche Ergänzungen der Karte, wie z.B. andere Sprachen, zusätzliche Orte oder Markierungskreuz, wenden Sie sich bitte an infografik@dw-world.de (-2566), Außerhalb der Bürozeiten an bilder@dw-world.de (-2555).*** DW-Grafik: Per Sander 2011_03_10_Laender_Prio_A_B
Korruption
ምስል DW

አርያም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሰ