የትራምፕ የእርዳታ ቅነሳ ዛቻ
ሰኞ፣ መጋቢት 25 2009ማስታወቂያ
የረሀብ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት ዓምደ መረብ በያዝነው የጎርጎሮሳውያኑ 2017 ፣ በ45 ሀገራት የሚገኙ 70 ሚሊዮን ያህል ሰዎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ሲል አስታውቋል። ይህን ያህል ህዝብ የአስቸኳይ እርዳታ ጠባቂ በሆነበት በዚህ ወቅት ላይ ብዙ እርዳታ አቅራቢ የሆነችው ዩናይትድ ስቴትስ የምትሰጠው መልስ ማሳሰቡ አልቀረም። የዚህም ምክንያቱ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሥልጣን ከያዙ በኋላ መንግሥታቸው ለተለያዩ ሀገራት የሚሰጠውን እርዳታ እንደሚቀንስ የሰነዘሩት ዛቻ ነው። ትራምፕ ያሉትን ተግባራዊ የሚያደርጉ ከሆነ ከአሜሪካን ከፍተኛ እርዳታ ስታገኝ በቆየችው በኢትዮጵያ ላይ ምን ዓይነት ተጽእኖ ያሳድር ይሆን ? የዋሽንግተን ዲሲው ዘጋቢያችን ስለ ጉዳዩ የኤኮኖሚ ምሁር አነጋግሯል ።
መክብብ ሸዋ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ