1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የታራሚዎች ቤተሰቦች ጥያቄ

ረቡዕ፣ ጳጉሜን 2 2008

ይህ የአባቷን እጣ ፈንታ ለማወቅ ዛሬ ወደ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ያመራች ልጅ ጥያቄ ነው። ጋዜጠኞች፤ፖለቲከኞች እና የሙስሊሞች መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ መሪዎች በእስር ላይ በሚገኙበት ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ባለፈው ቅዳሜ በእሳት የነደደበት ምክንያት ዛሬም ድረስ በውል አልታወቀም።

https://p.dw.com/p/1JxGt
Karte Äthiopien Amhara, Tigray, Oromia Deutsch

[No title]

የኢትዮጵያ መንግስት 23 ታራሚዎች በጥይት ተመተው እና በእሳት ተቃጥለው መሞታቸውን ቢያረጋግጥም ማንነታቸው እስካሁን አላሳወቀም። የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ግን በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የሞቱ ሰዎች ቁጥር መንግስት ከገለፀው በላይ ሳይሆን አይቀርም ሲሉ ይደመጣል። በእሳት ቃጠሎው የሞቱ ሰዎች ማንነት ለማወቅ ዛሬ ወደ ማረሚያ ቤቱ ያቀኑ የታራሚዎች ቤተሰቦች በጸጥታ ኃይሎች ተበትነዋል።
ዮሐንስ ገብረእግዚዓብሔር
እሸቴ በቀለ
ነጋሽ መሐመድ