የተባባሰዉ የሰብአዊ መብት ጥሰት በኢትዮጵያ
ረቡዕ፣ ግንቦት 3 2014ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሐገሪቱ ዉስጥ እየከፋ የመጣዉን የሰብአዊ መብት ጥሰት ለመከላከል እንዲጥርና መንግሥትን እንዲቆጣጠር የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጠየቀ።ኢሰመኮ ዛሬ ለተወካዮች ምክር ቤት የፍትሕና የዴሞክራሲ ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበዉ የ10 ወር ዘገባዉ እንዳለዉ በየጊዜዉ በሚያገረሹ ግጭቶች ምክንያት የሰብአዊ መብቶች ጥሰት እየጨመረ፣ ተጠያቂነትና የሕግ የበላይነት እየላላ ነዉ። ኮሚሽኑ አክሎ እንዳለዉ የመንግሥት የፀጥታ አካላት ከፍርድ ቤት ዉሳኔ ውጪ የሚፈፀምሙት ግድያ፣ ከመጠን ያለፈ የኃይል እርምጃ፣ የዘፈቀደ እሥር እና የፍርድ ቤት ትእዛዝ አለመከበር አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል።ምክር ቤቱ ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብሏልም-ኮሚሽኑ።
ሰለሞን ሙጪ
ነጋሽ መሐመድ
ማንተጋፍቶት ስለሺ