1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተቃውሞ ሰልፍ በበርሊን

ዓርብ፣ ግንቦት 1 2006

በኦሮምያ ክልል ለአዲስ አበባና ለኦሮምያ ልዩ ዞኖች የተዘጋጀውን ማስተር ፕላን በመቃወም ባለፈው ሳምንት ሰልፍ በወጡ በተለያዩ የኦሮምያ ክልልየሚገኙ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ላይ የተወሰደውን እርምጃ በመቃወም ዛሬ ጠዋት በርሊን ውስጥ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ።

https://p.dw.com/p/1BxKC
Demonstration gegen die Äthiopische Regierung in Berlin
ምስል Tewodros Lemmu

በተቃውሞ ሰልፉ ላይ የተካፈሉት ጀርመን ነዋሪ የሆኑ የኦሮሞ ተወላጆች በወቅቱ ለተፈፀመው የተማሪዎች ግድያ ተጠያቂ ነው ባሉት በኢትዮጵያ በመንግሥት ላይ ጫና እንዲያደርጉ ጠይቀዋል። የሰልፉ አዘጋጅ ኮሚቴ አባል አቶ ተስፋዬ አብዲሳ ለዶቼቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ ሰልፈኞቹ ተቃውሞአቸውንጥያቄዎችን የገለጹበትን ደብዳቤ ለጀርመን መንግሥት ለአውሮፓ ህብረትና ለፈረንሳይ መንግሥት ተወካዮች መስጠታቸውን ገልፀዋል። አቶ ተስፋዬን ሂሩት መለሰ አነጋግራቸዋለች።

በተመሳሳይ በዛሬዉ ዕለት የኢትዮጵያዉያን በብራስልስ የአዉሮፓ ኮሚሽን ፊት ለፊት በመገኘት የኢትዮጵያ መንግስት በዜጎቹ ላይ ይፈፅማል ያሉትን የሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ ግድያ፣ እስራትና ማፈናቀል አዉግዘዋል። ሰልፉ የተጠራዉ በዋናነት በአፋር የሰብዓዊ መብት ድርጅት ሲሆን ሉቅማን የኢትዮጵያ እና ቤልጅየም ሙስሊም ማኅበር እና በአዉሮጳ የኢትዮጵያ ግብረኃይል ለፍትህ የተባለ ድርጅትም ተባባሪ የሰልፉ አዘጋጆች መሆናቸዉ ተገልጿል። ተሰላፊዎቹን የቤልጅየም መንግስት የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተወካይ እንዳነጋገሯቸዉ እና ከአዉሮጳ ኮሚሽን ባለስልጣናት ጋ ለመነጋገርም ቀጠሮ የተያዘ መሆኑን የሰልፉ አስተባባሪ አቶ ጋዐዝ ኑር በብራስልስ ለዶቼ ቬለ ዘጋቢ ገበያዉ ንጉሤ ገልጸዋል።

ሂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ