1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተቃዋሚ ፓርቲዎች አቋምና አማራጭ መርሆዎች

እሑድ፣ ግንቦት 9 2007

ኢትዮጵያ ለአምስተኛዉ ብሔራዊ ምርጫ መሰናዶዋን እያገባደደች ነዉ።በየማሕበረ-መገናኛዉ ዜዴዎች የምናነባቸዉ አንዳድ ፁሁፎች «ዉጤቱ አስቀድሞ የታወቀ» እያሉ ቢተቹትም ገዢዉ ፓርቲም፤ ተቃዋሚዎቹም፤ አስመራጭ መራጮችም ለምርጫዉ መዘጋጀት፤መከራከር፤መነጋገራቸዉ እንደቀጠለ ነዉ።

https://p.dw.com/p/1FQvd
Addis Abeba Äthiopien Wahlen
ምስል Yohannes Gebereegziabher

በየክርክሮቹ እንደተሰማዉ ገዢዉ ፓርቲ ኢሕዴግ እስካሁን የሚከተለዉን መርሕ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ባለሥልጣናቱ እየገለጡ ነዉ።ተቃዋሚ ፓርቲዎች ባንፃሩ የገዢዉን ፓርቲ መርሕ አጥብቀዉ ይተቻሉ።ይሁንና እራሳቸዉ ተቃዋሚዎቹ በጋራ የሚወቅሱቱን ኢሕአዲግን በጋራ ለመታገል መሰባሰቡ ቀርቆ ወጥ አማራጭ መርሕ መያዛቸዉም እያጠያየቀ ነዉ።ለዚሕ ሳምንት እንወያይ ዝግጅታችንም የተቃዋሚ ፓርቲዎችን አቋም እና አማራጭ መርሆችን ይቃኛል።

ነጋሽ መሐመድ

ልደት አበበ