1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቦኑ ስደተኞች መንደር

ረቡዕ፣ መስከረም 12 2008

ከባየር ቀጥሎ ከፍተኛ ቁጥር የምታስናግደዉ የኖርድ ራይን ቬስት ፋለን ክፍለ ግዛት ናት።በግዚቲቱ አዲስ ከተቋቀሙት የስደተኞች ጊዚያዊ ጣቢያዎች አንዱ ስቱዲዮያችን ከሚገኝበት ከቦን ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኘዉ አዉሮጵፕን ጣቢያ ነዉ የተቋቀመዉ

https://p.dw.com/p/1Gbpb
የቦኑ ስደተኞች መንደር
ምስል picture-alliance/dpa/F. Gambarini

[No title]

የጀርመን ክፍለ-ግዛቶችም እንደ አዉሮጳ ሕብረት አባል መንግሥታት በድምፅ ብልጫ ሳይሆን በፍላጎት ስደተኞችን ተከፋፍለዉ እያስተናገዱ ነዉ።በደቡብ ምሥራቅ አዉሮጳን አቋርጠዉ ወደ ጀርመን የሚገቡት ሥደተኞች መጀመሪያ የሚረግጧት የደቡባዊ ጀርመንዋ ግዛት ባየር በርካታ ስደተኞች በማስተናገድ የመጀመሪያዉን ደረጃ ይዛለች።ከባየር ቀጥሎ ከፍተኛ ቁጥር የምታስናግደዉ የኖርድ ራይን ቬስት ፋለን ክፍለ ግዛት ናት።በግዚቲቱ አዲስ ከተቋቀሙት የስደተኞች ጊዚያዊ ጣቢያዎች አንዱ ስቱዲዮያችን ከሚገኝበት ከቦን ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኘዉ አዉሮጵፕን ጣቢያ ነዉ የተቋቀመዉ።ጣቢያዉ ትናንት የመጀመሪያዎቹን ስደተኞች ሲቀበል ሐይንሪሽ ዳንየል ተከታትሎ የዘገበዉ ይልማ ኃይለ ሚካኤል እንደሚከተለዉ አጠናቅሮታል።

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

ነጋሽ መሐመድ