1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅትና CPJ

ረቡዕ፣ ግንቦት 8 2004

የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ስላጉዳዩ ማብራሪያ እንዲሰጥ የአዲስ አበባው የዶቼቬለ ወኪል ታደሰ እንግዳው ጠይቆ ነበር ። ሆኖም ድርጅቱ መልስ የሚሰጠው በጉዳዩ ላይ ከጋዜጣ አሳታሚዎች ጋር ከተወያየ በኃላ መሆኑን ለወኪላችን አስታውቋል

https://p.dw.com/p/14wgv
CPJ logo, COMMITTEE TO PROTECT JOURNALISTS, graphic element on white 2008/11/26
ምስል APTN

ዓለም ዓቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት CPJ የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት በጋዜጣ አሳታሚዎች ላይ የሚያደርሰውን ጫና ተቃወመ ። CPJ ማተሚያ ቤቱ ለህትመት በሚመጡ ጋዜጦች ላይ የሚወጡ ፅሁፎችን አሳታሚዎች ቅድሚያ ምርመራ እንዲያደርጉባቸው የሚያዝ መመሪያ ማውጣቱ የፕሬስ ነፃነትን የሚፃረር ነው ብሏል ። ዶቼቬለ ያነጋገራቸው የ CPJ የአፍሪቃ ጉዳዮች ባለሞያ የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት በጋዜጠኝነት ላይ የቅድሚያ ምርመራ ጫና እያደረገ ነው ሲሉ ተቃውሞአቸውን ተናግረዋል ። አበበ ፈለቀ ከዋሽንግተን ዲሲ ዝርዝሩን ልኮልናል


የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ስላጉዳዩ ማብራሪያ እንዲሰጥ የአዲስ አበባው የዶቼቬለ ወኪል ታደሰ እንግዳው ጠይቆ ነበር ። ሆኖም ድርጅቱ መልስ የሚሰጠው በጉዳዩ ላይ ከጋዜጣ አሳታሚዎች ጋር ከተወያየ በኃላ መሆኑን ለወኪላችን አስታውቋል ።

አበበ ፈለቀ

ሒሩት መለሰ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ