የብሪታንያ ፖለቲካዊ ቀዉስ
ሐሙስ፣ ነሐሴ 30 2011ማስታወቂያ
ብሪታንያ ከአዉሮጳ ሕብረት አባልነት የምትወጣበት ሥልትና ጊዜ የሐገሪቱን ፖለቲከኞች አሁንም እንዳወዛገበ ነዉ።የጠቅላይ ሚንስትርነቱን ስልጣን ባለፈዉ ሐምሌ የያዙት ቀኝ አክራሪዉ ፖለቲከኛ ቦሪስ ጆንሰን ከአዉሮጳ ሕብረት ስምምነት ዉጪ ሐገራቸዉን ከሕብረቱ አባልነት ለማስወጣት የሸረቡት ሴራ እራሳቸዉን መልሶ እያዳጣ፣እያሟላጣቸዉ ነዉ።ጠቅላይ ሚንስትሩ እንዲዘጋ በሐገሪቱ ንግሥት ያስወሰኑበት የሐገሪቱ ምክር ቤት፣ ብሪታንያ ከምክር ቤቱ ይሁንታና ዕዉቅና ዉጪ ከሕብረቱ አባልነት እንዳትወጣ አግዷል።ጠቅላይ ሚንስትሩ ጥቅምት መጀመሪያ ላይ አጠቃላይ ምርጫ እንዲደረግ ያወጁትንም ዕቅድ ምክር ቤቱ ዉድቅ አድርጎታል።
ድልነሳ ጌታነሕ
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሰ