1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጠቅላይ ሚኒስትሯ አዲስ መንግስት ሊመሰርቱ ነዉ።

ዓርብ፣ ሰኔ 2 2009

ወይዘሮ ቴሬሳ ሜይ የሚመሩት ወግ አጥባቂዉ ፓርቲ በፊት ከነበረዉ መቀመጫ  በአስራ-ሁለት የቀነሰ ዉጤት አግኝቷል።ከፍተኛ ሽንፈት ይገጥመዋል የተባለዉ ዋነኛዉ ተቃዋሚ የሌበር ወይም የሠራተኛ ፓርቲ ባንፃሩ ተጨማሪ ሠላሳ መቀመጫዎችን አግኝቷል።

https://p.dw.com/p/2eQ4T
II. London Theresa May und Ehemann
ምስል Reuters/T. Melville

(Q&A) GB wahl ergebnisse - MP3-Stereo

                           

ብሪታንያ ዉስጥ ትናንት የተደረገዉ የምክር ቤት አባላት ምርጫ ያልታሰበ  ዉጤት ታይቶበታል።የሐገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር ወይዘሮ ቴሬሳ ሜይ የሚመሩት ወግ አጥባቂዉ ፓርቲ በፊት ከነበረዉ መቀመጫ  በአስራ-ሁለት የቀነሰ ዉጤት አግኝቷል። ከፍተኛ ሽንፈት ይገጥመዋል የተባለዉ ዋነኛዉ ተቃዋሚ የሌበር ወይም የሠራተኛ ፓርቲ ባንፃሩ ተጨማሪ ሠላሳ መቀመጫዎችን አግኝቷል።

Britannien Wahlen 2017 - BBC - Jeremy Corbyn
ምስል Getty Images/AFP/S. Rousseau

ወግ አጥባቂዋ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሪዛ ሜይ ትናንት በሀገሪቱ በተካሄደዉ የፓርላማ ምርጫ ፓርቲያቸዉ አብላጫ ድምጽን ባያገኝም አዲስ መንግሥት ለመመስረት እንደሚፈልጉ ገለፁ። ጠቅላይ ሚኒስትሯ ይሄን የገለፁት ዛሬ ከንግስት ኤልዛቤት ሁለተኛ ጋር ከተነጋገሩ በኋላ ነዉ። ቴሬዛ ሜይ ብሪታንያ ከአዉሮጳ ኅብረት ስለመዉጣትዋ ያላቸዉን አቋም አጠናክረዋል። 
«ይህ እንደ ሀገር አንድ ላይ እንድንሆን ያስችለናል። ኃያላችንንም በዚህ ሀገር ላሉ ሁሉ ለሚሠራ ለስኬታማ የብሬክዚት ውል እንድናውለው እና ከአውሮጳ ኅብረት ጋር ለረዥም ጊዜ ብልጽግናችን ዋስትና የሚሰጥ፣ አዲስ አጋርነትን ለማረጋግጥ ያስችለናል። ባለፈው ሰኔ ህዝቡ ድምጹን የሰጠው ለዚህ ነው። ይህን ነው እኛም የምናቀርበው። አሁን ወደ ሥራ እንግባ።»    
የአዉሮጳ ኅብረት ባቀረበዉ እቅድ መሠረት ብሪታንያ ከአዉሮጳ ኅብረት የመዉጣትዋ ሂደት ሰኔ 12 ይጀምራል። ትናንት በተካሄደዉ የፓርላማ ምርጫ የጠቅላይ ሚኒስትሯ ወግ አጥባቂዉ ፓርቲ 315 ወንበር ብቻ ነበር ያገኘዉ። ይህ ቁጥር ካለፈዉ ጋር ሲነፃፀር በ 12 መቀመጫ ያነሰ ነዉ። አብላጫ ድምጽን ለማግኘት 326 የፓርላማ ወንበር ማግኘት ያስፈልጋል። የነፃ ዲሞክራቶችም ፓርቲ ከፊቱ በተሻለ ሁኔታ የፓርላማ መቀመጫዉ ቁጥር በ 12  ከፍ ብሎአል። የምርጫዉን ዉጤት ያወደሱት የሠራተኛዉ ፓርቲ ፖለቲከኛ ጀምስ ኮርብያን ሕዝብ የቁጠባ ፖለቲካ ይብቃን ብሎአል ሲሉ ነዉ የተናገሩት።  
«ታውቃላችሁ ፖለቲካ ተቀይሯል፤እናም ፖለቲካ ቀድሞ የነበረበት ሳጥን ውስጥ ተመልሶ አይገባም። ምክንያቱም የሆነው ምንድነው ህዝቡ የቁጠባ ፖለቲካ በቅቶናል እያለ ነው። ለህዝብ ወጪ የሚደረግ ገንዘብ ቅነሳ ለጤና ፣ ለትምህርት ቤቶች እና ለትምህርት አገልግሎቶች የገንዘብ ድጋፍ ማነስ እንዲሁም ወጣቶቻችን በህብረተሰቡ ውስጥ የሚገባውን እድል አለማግኘታቸው ይብቃ እያለ ነው ። ፓርቲየ ለጥቂቶች ሳይሆን ለብዙዎች ባወጣው የፖለቲካ መርህ ላይ ባካሄደበትዘመቻ በጣም ኮርቻለሁ።ለቁጠባ ጀርባቸውን ሰጥተው ለተስፋ ፣ለወደፊቱ ተስፋ ድምጻቸውን በሰጡት  ውጤትም በጣም እኮራለሁ ።»
 የስኮትላንድ ብሔራዊ ፓርቲ ከባድ ሽንፈት ደርሶበታል። የወንበር ቁጥርም ከ 56 ወደ 35 አሽቆልቁልዋል። በዚህም ምክንያት ብሪታንያ ዉስብስብ የሆነ የካቢኔ አወቃቀር ይጠብቃታል። ከምርጫዉ ዉጤት በኋላ የፖለቲካ ጉዳይ ምሁራን ቴሪዛ ሜይ ስልጣናቸዉን ሊለቁ እና አዲስ ምርጫ ሊካሄድ ይችላል የሚል ግምት ሰጥተዉ ነበር። ሜይ ባለፈዉ ሚያዝያ ትናንት የተካሄደዉን የፓርላማ ምርጫ  እንዲደረግ ጥሪ ያቀረቡበት በፓርላማ ያላቸዉን ድምጽ ከፍ በማድረግ ከአዉሮጳ ኅብረት ጋር የሚያደርጉትን ድርድር ስኬታማ እንዲሆን በማሰብ ነበር። 
ጠቅላይ ሚንስትር ሜይ አስቸኳይ ምርጫ የጠሩት ፈፁም አብላጫ ድምፅ በማግኘት ጠንካራ መንግሥት ለመመሥረት ነበር።  የምርጫዉን ዉጤትና የከእንግዲሁን ሂደት በተመለከተ የለንደን ወኪላችን በስልክ አነጋነዋል።

Arlene Foster, Parteichefin der nordirischen DUP
ምስል Getty Images/AFP/P. Faith
Schottland Nicola Sturgeon
ምስል Reuters/R. Cheyne

ድልነሳ ጌታነሕ

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ