1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቤኔዲክት 16ኛ ሥንብት

ሐሙስ፣ የካቲት 21 2005

የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክት 16ኛ፤ ዛሬ ማታ በመሃል አውሮፓ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 8 ሰዓት ላይ በኢትዮጵያ ከምሽቱ 4 ሰዓት ላይ ፤ በገዛ ፈቃዳቸው ሥልጣን የሚለቁበት ጊዜ ያከትማል።

https://p.dw.com/p/17mwp
ምስል Reuters

 ከዚያ 3 ሰዓት ቀደም ብለው በሄሊኮፕተር ወደ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ መኖሪያ ካስቴል ጋንዶልፎ እንደሚጓዙና በዚያ ለ2 ወራት እንደሚቀመጡ ተነግሯል። ከዚያ በኋላ፤ በቫቲካን ወደሚገኝ አንድ ገዳም ይዛወራሉ።  የ 85 ዓመቱ አዛውንት ፣ ቤኔዲክት 16ኛ ፤  ዛሬ በሮማ ካርዲናሎችን የተሰናበቱ ሲሆን፤ ። ካርዲናሎቹም ለረጅም ጊዜ  በማጭብጨብ አጸፋውን መልሰውላቸዋል።
ጀርመን ውስጥ፤ ስንብታቸውን መንስዔ በማድረግ፤ በብዙዎቹ የካቲሊክ አብያተ-ክርስቲያን ደወል ይደወላል። በርሊን ውስጥም በቅድስት Hedewig ካቴድራል፣ መራኂተ-መንግሥት አንጌላ ሜርክል በሚገኙበት  ሥርዓተ ጸሎት ይደረጋል ተብሏል። 

ርዕሠ-ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክት አስራ-ስድሰተኛ ዛሬ የቤተ-ክርስቲያኒቱን ምዕመናን በይፋ ተሰናብተዋል።  ከቀተር በፊት ቫቲካን አደባባይ በተከናወነዉ የሥንብት ሥነ-ሥርዓት ላይ አንድ መቶ ሺሕ የተገመተ ምዕመን ተገኝቶ ነበር።ከሥምንት ዓመት በፊት የርዕሠ ሊቀነ-ጳጳሳትነቱን ሥልጣን የተረከቡት ቤኔዲክት አስራ-ስድሰተኛ ሥልጣናቸዉን በፈቃዳቸዉ መልቀቃቸዉን ባስታወቁት መሠረት ነገ-መንበራቸዉን በይፋ ይለቃሉ።በሮማ ካቶሊካዊት የሰባት መቶ ዓመታት ታሪክ አንድ ርዕሠ-ሊቃነ ጳጳሳት ሥልጣኑን በፈቃዱ ሲለቅ ቤኔዲክት አስራ-ስድስተኛ የመጀመሪያዉ ናቸዉ።

Papst Benedikt erreicht die Sommerresidenz Castel Gandolfo
ምስል VINCENZO PINTO/AFP/Getty Images

ቤኔዲክት 16 ተኛ በቫቲካኑ የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተገኙት ምዕመናን ባሰሙት የመጨረሻ ንግግራቸው ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳስነት የወረዱት ለቤተክርስቲያኗ መልካሙን ሁሉ በማሰብ መሆኑን ገልፀው  በመፃኤ እድሏም ላይ ትልቅ እምነት እንዳላቸው አስታውቀዋል ። ተተኪያቸውን ለሚመርጡት ካርዲናሎችም ህዝቡ በፀሎት እንዲተጋ አሳስበዋል ። ያሳለፉት ጊዜ ደስታና ብርሃን የተንፀባረቀበት ብቻ ሳይሆን በቤተክርስቲያኒቱ ታሪክ ማዕበልና ንፋሱ ያያለበትም ወቅት እንደነበረ አስታውሰዋል ። ችግሩ አሁንም እንዳለ ሳይጠቁሙ አላለፉም ።
« በቤኔዲክት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስነት ዘመን የደስታ ጊዜ እንደነበር ሁሉ በርካታ አስቸጋሪ ወቅቶችም ገጥመዋል ። በአሁኑ ሰአት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ችግር ውስጥ ናት ። ሆኖም እግዚአብሄር በስተመጨረሻ ፍርዱን ይሰጣል ። »የቤኔዲክት 16 ተኛ ንግግር ህዝቡ ሲያጨበጭብና ስማቸውንም በየመካከሉ ሲጠራ በተደጋጋሚ ይቋረጥ ነበር ።  የመሰናበቻ ንግግሩን ለመከታተል በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የተገኙት ምዕመናን ቁጥር ከ 150 ሺህ በላይ እንደነበር ሮይተርው የዜና ወኪል ዘግቧል ።ሥለ ዛሬዉ የሥንብት ሥርዓትና ሥለ ተከታዩ ምርጫ የቫቲካን ወኪላችንን ተኽለእግዚ ገብረኢየሱስን በስልክ አነጋግሬዋለሁ። 

 

ተኽለእግዚ ገብረኢየሱስ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ