1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቤልጂግ ፖሊስ ሁለት ተጠርጣሪዎች ያዘ

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 19 2008

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአውሮጳ የፀረ-ሽብር ተልዕኮ ትኩረት የተደረገባት ቤልጅግ በአዲስ አመት ዋዜማ ጥቃት ለመሰንዘር ሳያቅዱ አይቀሩም ያለቻቸውን ሁለት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር አውላለች።

https://p.dw.com/p/1HVmX
Belgien Terrorismus Polizei Razzia Durchsuchungen Brüssel
ምስል picture-alliance/dpa/N.Maeterlinck

[No title]

የቤልጅግ ፖሊስ ባደረገው አሰሳ የጦር ሠራዊት የሚመስሉ አልባሳት እና የኮምፒውተር ቁሳቁሶች ማግኘቱን አስታውቋል። የአገሪቱ ባለስልጣናት አሁን በቁጥጥር ስር የዋሉት ግለሰቦች ከፓሪሱ የሽብር ጥቃት ጋር የሚያገናኛቸው አንዳች ነገር አለመኖሩን በአሰሳውም ምንም አይነት የጦር መሳሪያ አሊያም ተቀጣጣይ ቁስ አለመገኘቱን አስታውቀዋል።

ገበያው ንጉሴ

ሸዋዬ ለገሰ