1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቤልጂግ የአውሮፓ ሕብረት ፕሬዚደንትነትን ስልጣን መረከብ

ዓርብ፣ ሰኔ 25 2002

ቤልጂግ በየመንፈቁ የሚቀያየረውን የአውሮፓን ሕብረት ርዕስነት በዛሬው ዕለት ከስፓኝ ተረክባለች። አገሪቱ ሃላፊነቱን የተረከበችው በውስጣዊ ፌደራላዊ ችግሮች የተነሣ ገና ቋሚ መንግሥት መምረጥ ባልቻለችበት ሁኔታ ነው።

https://p.dw.com/p/O8OB
ምስል dpa

እርግጥ ሕብረቱ የውጭ ጉዳይ ተጠሪና ፕሬዚደንት ከመረጠ ወዲህ የመንግሥታቱ ሥራ መቃለሉ አልቀረም። ቢሆንም በሚቀጥሉት ወራት ቤልጂግን የሚጠብቃት ተግባር ያን ያህል ቀላል አይሆንም። ታዛቢዎች ቤልጂግ በጸና እግር ላይ እንዳልቆመች በማመልከት አውሮፓ በብራስልስ ርዕስነት ዘመን አዕምሮ-አልባ እንዳትሆን መስጋታቸውን ነው የገለጹት። በጉዳዩ የብራስልስ ወኪላችንን ገበያው ንጉሤን በስልክ አነጋግሬ ነበር።

ገበያው ንጉሤ

መሥፍን መኮንን

አርያም ተክሌ