1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቤልጂግ ምርጫ ና የመንግስት ምስረታ ድርድር

ማክሰኞ፣ ሰኔ 8 2002

በዘውድ የበላይ ጠባቂነት በምትደዳደረው በቤልጂግ በዕሁዱ ምርጫ በደች ተናጋሪዎቹ በፍላንደሮች ፌደራዊ ክፍለ ሀገር ብሔረተኛው የፍሌሚሾች ጥምረት ሲያሸንፍ ፤ በደቡቡ የዋሎንያ ፌደራዊ ክፍለ ሀገር ደግሞ የሶሻሊስቶቹ ፓርቲ አብላጫውን ድምፅ አግኝቷል ።

https://p.dw.com/p/NrdD
ባርት ደ ዌቨርምስል AP

ይሁንና ፍሌሚሾችን ከደቡቦቹ ከዋሎኖች የመገንጠል አቋም የያዘው የብሔረተኞቹ ፓርቲ ከሀገሪቱ ምክር ቤት አብላጫውን መቀመጫ ማሸነፉ ቤልጅየም ለሁለት የመከፈል አደጋ ላይ ናት የሚል ስጋት ጭሯል ። ይሁንና እነዚህ ፓርቲዎች በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የተራራቀ አቋም ቢኖራቸውም ጥምር መንግስት ለመመስረት የሚያስችላቸውን ድርድር ጀምረዋል ። ድርድሩ መቼ እንደሚሳካ ከአሁኑ ለመገመት አስቸጋሪ ነው ።

ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ