1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቡሄ በአል

ረቡዕ፣ ነሐሴ 21 2000

ቡሄ መጣ ያ መላጣ ቅቤ ቀቡት እንዳይነጣ ቡሄ በሉ ልጆች ሁሉ እያልን ሆ ስንል ከዋቂዎች ስጦታን ስናገኝ ደስታችን ልዩ ነዉ

https://p.dw.com/p/F5sD
ኢትዮጽያዉያን ህጻናት በፍራንክፈርት በኢትዮጽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን በክበረ በአል ላይምስል DW

የቡሄ በአል የክረምቱ ማለቅያ ነሃሴ አስራ ሁለት አስራ ሶስት አካባቢ ሲከበር ቡሄ ካለፈ የለም ክረምት ዶሮ ከጮኸ የለም ለሊት ይባላል። የቡሄ በአል ካለፈ በኻላ መስከረም ስለሚጠባ እና ብራ ስለሚሆን። ደስታ ተክለወልድ በጻፉት መዝገበ ቃላት ህጻናት በቡሄ እለት ሆ ብለዉ ዳቦ ለሰጣቸዉ ምስጋና ሲያቀርቡ የሚሉትን አስፍረዋል
ሃሚና ሃሚና
ዘነዘና የብር ዘነዘና
ጌታዪን ያማ ሰዉ
ነጭ እከክ ይዉረሰዉ!

ስለቡሄ አዋቂዎችን ጥይቀን፣ ሆያ ሆዪ ብለናል ያድምጡን