1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የበርሊን ግንብ የፈረሰበት ሀያኛ ዓመት

ሰኞ፣ ጥቅምት 30 2002

ልክ የዛሬ ሀያ ዓመት በዛሬዋ ዕለት በርካታ ጀርመናውያን ያላሰቡት ነገር ግን የዘወትር ምኞታቸው የነበረ እና እስከዛሬም እንደ ተዓምር የሚቆጥሩት ነገር እውን ሆነ ።

https://p.dw.com/p/KS8C
ምስል DW

ጀርመንን ለሁለት ከፍሎ የቆየው የበርሊን የግንብ አጥር ፈረሰ ። የዚህ ግንብ መናድ ለሁለቱ ጀርመኖች ውህደት መንገድ በመጥረግና በዓለም ዙሪያ የኮምኒዝምን ስርዓት መንኮታኮት በማፋጠን በዓለም ታሪክ ልዩ ቦታን ይይዛል ። ይህ ዕለትም ዛሬ በርካታ የዓለም መሪዎች በተገኙበት በዋና ከተማይቱ በበርሊን እየተከበረ ነው ። የበርሊኑ ዘጋቢያችን ይልማ ኃይለ ሚካኤል የዛሬ ሀያ ዓመት የሆነውን ወደ ኃላ መለስ ብሎ ያስቃኘናል ። ግንቡ ሲፈርስ የነበሩ ኢትዮጵያያንም ትውስታቸውን ያካፍሉናል ።

ይልማ ኃይለ ሚካኤል ፣ ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ