1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቀድሞው የቻድ መሪ ሐብሬና ሴኔጋል

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 17 2004

ዴን ሀግ የሚገኘው አለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍ/ቤት ሴኔጋል የቀድሞውን የቻድ ፕሬዚደንት ሒሴኔ ሀብሬ ባስቸኳይ ለፍርድ እንድታቀርብ፣ ይህን ካላደረገች ግን ችሎታቸው በቤልጅየም እንዲጀመር ለዚችው አገር እንድታስረክብ ካዘዘ በኋላ የአፍሪቃ ህብረት እና ሴኔጋል በጉዳዩ ላይ ምክክር ይዘዋል።

https://p.dw.com/p/15db7
Das undatierte Archivbild zeigt den Ex-Präsidenten des Tschad, Hissene Habre. Menschenrechtler in Afrika wollen Habre, den Ex-Machthaber des Sahelstaates Tschad, vor Gericht bringen. «Habre ist Afrikas Pinochet», sagte in Dakar Reed Brody von der internationalen Menschenrechtsorganisation Human Rights Watch. Während Habres Regierungszeit (1982-1990) sollen nach Angaben einer Wahrheitskommission 40 000 Menschen aus politischen Gründen ermordet und 200 000 gefoltert worden sein. Habre (57) lebt im Exil in der senegalesischen Hauptstadt Dakar. dpa (zu dpa 0007 vom 28.01.2000)
ሒሴኔ ሀብሬምስል picture-alliance/dpa

ሀብሬ እአአ ከ 1982-1990 በሥልጣን በቆዩበት ዓመታት ሀገራቸው በአሥር ሺህ የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎቻቸውን ገደለዋል፣ የቁም ሥቅል አሳይተዋል በሚል ክስ እንዲመሠረትባቸው ፍርድ ቤቶች እና መንግስታት ከፍተኛ ጥረት ቢያደርጉም፤ ሀብሬ ከ20 አመት በላይ በነፃ ሴኔጋል ውስጥ ከኖሩ በኋላ ነበር ከሰባት ዓመት በፊት በቁም እሥር የዋሉትና የዴን ሀጉ አለም አቀፉ ፍ/ቤት ሀብሬ በሴኔጋል ፍርድ እንዲቀርቡ ባለፈው ዓርብም የወሰነው ። ሌስሊ ሀስኬል፤ የሰብዓዊ ተሟጋቹ ድርጅት ሂውማን ራይትስ ዎች ጠበቃ የዴን ሀጉን አለም አቀፉ ፍ/ቤት ውሳኔ በመደገፍ ድል የሚታይበት ሰዓት መቃረቡን አብስረዋል።

« ዛሬ ሴኔጋላውያን እና የአፍሪቃ ህብረት ባለው የሴኔጋል የፍትህ አውታር ውስጥ የሀብሬን ችሎት የሚከታተል አንድ ልዩ ፍርድ ቤት ማቋቋም ስለሚቻልበት ጉዳይ ዳካር ውስጥ ውይይት ጀምረዋል። የዴን ሀጉ ውሳኔ በአሁኑ ጊዜ መደረሱ በሀብሬ ጉዳይ ላይ ወሳኝ ውጤት ያስገኛል ብዬ አስባለሁ። » የሴኔጋል የፍትህ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማርሴክ ሜንዲ ለ ፈረንሳይ ዜና ወኪል እንደገለፁት፣ ፍርድ ቤቱ የውጭ እና የሴኔጋል ዳኞችን ያቀፈ ይሆናል።

ሴኔጋል የተባበሩት መንግስታት ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዳካር የሚኖሩትን የ69 አመት የቀድሞ መሪ ሀብሬን ለፍርድ እንድታቀርብ አልያም ለቤልጅየም እንድታስረክብ ባለፈው አርብ ባስተላለፈው ትዕዛዝ ተስማምታለች።

Former Chad dictator Hissene Habre seen as he leaves the court in Dakar, Senegal, on Friday, Nov. 25, 2005.The former dictator was likely to be freed after a Senegalese court said Friday it had no jurisdiction to rule on his extradition to Belgium to stand trial for war crimes.Belgium had issued an international arrest warrant for Habre under its "universal jurisdiction" laws, which allow for prosecutions for crimes against humanity wherever they were committed. (ddp images/AP Photo/Schalk van Zuydam)
ምስል AP

እኢአ 2006 ዓም ሴኔጋል የአፍሪቃ ህብረትን ጥያቄ በመከተል ሀብሬ ለፍርድ እንዲቀርቡ ያደረገችው ድርድር ሳይሳካ ቀርቷል። የተባበሩት መንግስታት ሀብሬን በወቅቱ አሳልፎ ለቻድ መንግስት መስጠት አግባብ አይሆንም በማለት አጣጥሎታል። ይሁን እና ሴኔጋል በአብዱላይ ዋድ የአገዛዝ ዘመን በተደጋጋሚ አቋሟን እንደቀየረች መቀመጫው ለንደን የሚገኘው አለም አቀፍ የህግ ባለሙያዎች ማህበር ዋና ሀላፊ ማርክ ኤሊስ ያስታውሳሉ፤

« በርግጥ ሴኔጋል ሀብሬን ለፍርድ ማቅረቧን ጠብቀን ማየት ይኖርብናል። በርካታ ጊዜ ይህንን እንደሚያደርጉ ተናግረው ነበር። ግን እስካሁን ድርስ ይህን አላደረጉም። ምናልባት የአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍ/ቤት አሁን ካሳለፈው አሳሪ ውሳኔ በኋላ ሴኔጋል አስፈላጊውን ርምጃ ትወስድ ይሆናል።»

ሰኔ መጀመሪያ ላይ የሀብሬን ጉዳይ የሚመለከት አንድ ቡድን ሴኔጋል ውስጥ ጉዳዩን ሲከታተል ቆይቷል። የሴኔጋል ፍትህ ሚኒስቴር እንደገለጸው፤ ሲኔጋል በሳምንቱ መጨረሻ ከአፍሪቃ ህብረት ጋ ያደረገችው ምክክር በርግጥ ሀብሬን ለፍርድ ለማቅረብ መወሰኗን ማሳመኛ ይሆናል ።

ሀብሬ ለ8 በሥልጣን በቆዩበት ዓመታት ለ 40 000 የፖለቲካ ግድያ እና ለ 200 000 እስራት እና እንግልት ተጠያቂ እንደሆኑ ይነገራል። በመፈንቅለ መንግስት ከሥልጣን የተውገዱትና በወደ ሴኔጋል የሸሹት ሀብሬ ባልተገኙበት እአአ 2008 በአገራቸው በተካሄደ ችሎት ፈፅመውታል ለተባለው ወንጀል የሞት ፍርድ ተበይኖባቸዋል። ሀብሬ ለፍርድ የሚቀርቡበት ርምጃ ለሌሎች ከሥልጣን ለተወገዱና በስደት ለሚኖሩ የቀድሞ መሪዎች የሚኖረውን ተፅዕኖ ማርክ ኤሊስ እንደሚከተለው ያስረዳሉ።

« ይህ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ውሳኔ ወደትክክለኛው መንገድ የሚያመራ ውሳኔ ይመስለኛል። ወንጀል የፈፀሙ የአገር መሪዎች ሸሽተው በሌላ አገር ተገን ጠይቀው የሚኖሩበት ጊዜ ያከተመለት ይመስለኛል። ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ይህን ግልፅ አድርጓል። እና ለፍርድ ይቀርባሉ። » የአፍሪቃ ህብረት እና ሴኔጋል የጀመሩት ውይይት ነገ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ልደት አበበ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ