1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቀይ መስቀል ድርጅት በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች

ዓርብ፣ የካቲት 30 2004

በዛሬው የወጣቶች ክፍለ ጊዜ ሁለት የቀይ መስቀል በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች እንግዳዎቻችን አድርገናል። ወጣቶቹ የመጀመሪያ ህክምና ሰጪ ሆነው ሲያገለግሉ አመታት ተቆጥረዋል። ስለ ስራቸው እና ገጠመኞቻቸው ከልደት አበበ ጋ በስልክ ቆይታ አድርገዋል።

https://p.dw.com/p/14FmG
Rotes Kreuz
ቀይ መስቀል

በዛሬው የወጣቶች ክፍለ ጊዜ ሁለት የቀይ መስቀል በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች እንግዳዎቻችን አድርገናል። ወጣቶቹ የመጀመሪያ ህክምና ሰጪ ሆነው ሲያገለግሉ አመታት ተቆጥረዋል። ስለ ስራቸው እና ገጠመኞቻቸው ከልደት አበበ ጋ በስልክ ቆይታ አድርገዋል።

Bildergalerie 150 Jahre Rotes Kreuz Henri Dunant 1
የቀይ መስቀል መስራች ሔንሪ ዱና (1828-1910)ምስል ullstein bild - Roger Viollet

­

ወጣት መሳይ ፍቃዱ እና ምንያህል አባትነህ በአዲስ አበባ የቀይ መስቀል ቅርንጫፍ የመጀመሪያ ህክምና ይሰጣሉ። ይህንንም አገልግሎት የሚሰጡት በበጎ ፍቃደኝነት ነው።ሁለቱም የ21 ዓመት ወጣት ናቸው። ይህ ሙያ ሁልጊዜ ካልተጠበቀ አደጋ ጋ የተያያዘ ነው። እንዲሁም የአዕምሮ ጥንካሬን ይጠይቃል። ዋናው ነገር ትዕግስት ነው ይላል መሳይ። ምንያህል ደግሞ ቆራጥነት!

ጀርመን ውስጥ አደጋ በደረሰበት ቦታ አስቀድሞ የተገኘ ሰው የመጀመሪያ ህክምና የመስጠት ግዴታ አለበት። ይህን በተመለከተ ወጣቶቹ እስካሁን በሚኖሩበት አዲስ አበባ ምን ታዝበው ይሆን? ለዚህ እና ለሌሎች ጥያቄዎች ወጣቶቹ መልስ ሰጥተውናል።

ከድምፁ ዘገባ ያገኙታል።

ልደት አበበ

ተክሌ የኋላ