1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቀይ መስቀል እርዳታ ጥሪ

ሰኞ፣ ጥር 9 2008

ማህበሩ በሃገሪቱ በድርቅ ለተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች አስቸኳይ እርዳታ ለመለገስ የሚፈልጉ እርዳታቸውን በባንኮች በስልክና በሌሎችም የመገናኛ አገልግሎቶች መስጠት እንደሚችሉም ጥሪ አስተላልፏል ።

https://p.dw.com/p/1HfbZ
Äthiopien, Rotes Kreuz
ምስል DW/G. Tedla
Äthiopien, Rotes Kreuz
ምስል DW/G. Tedla

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ፣ኢትዮጵያውን የመታው ድርቅ የምግብ እጥረት ባስከተለባቸው በአፋርና በሶማሌና በምሥራቅ ሐረርጌ አካባቢዎች እርዳታ መስጠት መጀመሩን አስታወቀ ። የድርጅቱ ሃላፊ ለዶቼቬለ እንደተናገሩት የመንግሥትም ሆነ የሌሎች በጎ አድራጊ ድርጅቶች አቅም እስከሚጠናከር ቀይ መስቀል በነዚህ አካባቢዎች ቀድሞ ለመድረስ በመወሰን አስቸኳይ እርዳታ እየሰጠ ነው ።

ማህበሩ በሃገሪቱ በድርቅ ለተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች አስቸኳይ እርዳታ ለመለገስ የሚፈልጉ እርዳታቸውን በባንኮች በስልክና በሌሎችም የመገናኛ አገልግሎቶች መስጠት እንደሚችሉም ጥሪ አስተላልፏል ። በጉዳዩ ላይ የማህበሩን ዋና ፀሃፊና የህዝብ ግንኙነት አስተባባሪን የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ አነጋግሯል።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ