1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ሽብርተኝነት

በመኪና የሽብር ጥቃት በለንደን

ሰኞ፣ ሰኔ 12 2009

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እንደሚታየዉ የሽብር ጥቃት አድራሾች የንጹሐንን ሕይወት ለመቅጠፍ የጦር መሣሪያ ቃታ መሳብን ወይም በፈንጂ ነጉደዉ ማንጎድን ብቻ ሳይሆን ተሽከርካሪዎችንም ባለ ኃይላቸዉ እያከነፉ ጉዳት ማድረሱን ሥራዬ ብለዉታል። ትናንት ምሽቱን ለንደን ላይም የሆነዉ ይኸዉ ነዉ።

https://p.dw.com/p/2exSr
England London Finsbury Park Moschee mutmaßlicher Anschlag auf Muslime
ምስል Reuters/K. Coombs

M M T/ Beri. London (London attack) - MP3-Stereo

በሰሜናዊ ለንደን በሚገኝ መስጊድ ጾማቸዉን ፈትተዉ ጸሎታቸዉን አድርሰዉ የሚመለሱ የከተማዋ ሙስሊም ነዋሪዎች ፖሊስ ሆን ተብሎ እንደተፈፀመ በጠረጠረዉ የመኪና ግጭት ጉዳት ደርሶባቸዋል። አንድ ሰዉ ሕይወቱ አልፏል። ጉዳት ከደረባቸዉ 10 ሰዎች የሁለቱ ከበድ እንደሚል ተነግሯል። እሳት ባስከተለዉ አደጋ ከሃዘን ያልተላቀቀችዉ የብሪታንያ ዋና ከተማ ለንደን ትናንት ማምሻዉን ደግሞ በመኪና ጥቃት ተደናግጣለች። ሃና ደምሴ ከለንደን ተከታዩን ዘገባ ልካለች።

ሃና ደምሴ

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ