1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሶርያ ስደተኞች እና ዩኤስ አሜሪካ

ሐሙስ፣ ኅዳር 9 2008

በፈረንሳይ ፓሪስ የሽብር ጥቃት ካደረሱት ሰዎች መከከል አንደኛው ከሶርያ ስደተኞች ጋር ተመሳስሎ ወደ አውሮፓ ሳይገባ አልቀረም መባሉን ተከትሎ የሬፓብሊካን ፓርቲ ፖለቲከኞች የሶሪያ ስደተኞች ወደ ዩናይትድ ስቴትስ እንዳይገቡ በመጠየቅ ላይ ናቸው።

https://p.dw.com/p/1H90G
Barack Obama beim Asia-Pazifik-Forum in Manila
ምስል picture-alliance/dpa

[No title]

ቴድ ክሩዝ እና ጄብ ቡሽን የመሳሰሉ የሬፓብሊካን ፓርቲ የ 2016 ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እጩ ተፎካካሪዎች ደግሞ የኦባማ አስተዳደር ለክርስቲያን ሶርያውያን ስደተኞች ብቻ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ የመግብያ ፈቃድ ሊሰጥ ይገባል ሲሉ ተደምጠዋል። የፕሬዝዳንት ኦባማ አስተዳደር ግን ስደተኞቹ አስፈላጊውን የምርመራና ማጣሪያ መስፈርት አሟልተው ወደ ሀገሪቱ የሚገቡ በመሆናቸው አሸባሪዎች ሰርገው ሊገቡ የሚችሉበት እድል የለም ይላል። አብዛኛውን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ኮንግረስ ወንበር የተቆጣጠሩት የሬፓብሊካን ፓርቲ አባላት ስደተኞቹ ወደ ሀገሪቱ እንዳይገቡ የሚያግድ ረቂቅ ህግ ለማጽደቅ ለዛሬ ቀጠሮ የያዙ ሲሆን ከዋይት ሀውስ የሚወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ፕሬዝዳንቱ ረቂቅ ህጉን ይቀለብሳሉ ተብሏል።

ናትናኤል ወልዴ

አርያም ተክሌ

አዜብ ታደሰ