1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሶርያ ርዳታ አሰባሳቢ ጉባዔ

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 17 2010

ካለፉት ሰባት ዓመት በላይ በርስ በርስ ጦርነት ላይ ለምትገኘው ሶርያ ርዳታ ለማሰባሰብ በብራስልስ ቤልጅየም የተጠራው የሁለት ቀናት ጉባዔ ዛሬ ተጠናቀቀ። በዚሁ በተመድ እና በአውሮጳ ህብረት የተጠራው ጉባዔ ላይ ከ80 የሚበልጡ የመንግሥታት እና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች ተሳትፈዋል።

https://p.dw.com/p/2weXX
Syrien-Geberkonferenz in Brüssel
ምስል Getty Images/AFP/E. Dunand

« ጉባዔው የዠኔቩን የሰላም ውይይት እንደገና የማነቃቃት ዓለማም አለው።»

ለሶርያ ርዳታ ለማሰባሰብ በብራስልስ ቤልጅየም የተጠራው የሁለት ቀናት ጉባዔ ዛሬ ተጠናቀቀ። በጉባዔው የተካፈሉት ወገኖች 4,4 ቢልዮን ዶላር ርዳታ ለመስጠት ቃል ገብተዋል። እርግጥ፣ የጉባዔው ዋና ዓላማ ለ13 ሚልዮን ሶርያውያን ርዳታ ለማሰባሰብ ቢሆንም፣ የሶርያን ውዝግብ ለማብቃት የሚጥረውን የዠኔቩን ድርድር እንደገና ለማስጀመር ያለመም መሆኑን የአውሮጳ ህብረት የውጭ ጉዳይ ተጠሪ ፌዴሪካ ሞጌሪኒ ገልጸዋል።

ገበያው ንጉሤ

አርያም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሠ