1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሶማሊያ ፖሊሶች መጥፋትና እንድምታው

ሰኞ፣ ሐምሌ 26 2002

በጀርመን መንግስት በተሰጠ የ1ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ በኢትዮዽያ የሰለጠኑ 1ሺህ ያህል ፖሊሶች ደብዛቸው ጠፋ።

https://p.dw.com/p/OaHm
ምስል DW

በኢትዮዽያ ሁርሶ ማሰልጠኛ ጣቢያ ለሁለት ወራት ስልጠና የወሰዱ 1ሺህ ያህል የሶማሊያ ፖሊሶች በእርግጥ ከኢትዮዽያ ምድር ወጥተዋል። ሞቃዲሾ ግን አልደረሱም። እንደብዙዎች እምነት ፖሊሶቹ አክራሪ ቡድኖችን ሳይቀላቀሉ አይቀርም። የጀርመን መንግስት የበጀት ድጋፍ በኢትዮዽያ የሰለጠኑት የሶማሊያ ፖሊሶች ደባዛቸው የመጥፋት ጉዳይ እያነጋገረ ነው። በተለይም ጀርመን ስልጠናውን በተመለከተ ለመንግስታቱ ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት አለማሳወቋ ሁለቱን ወገኖች እያሟገተ ይገኛል። ስልጠናው በኢትዮዽያ እንዲሰጥ መደረጉ ሌላው ችግር እንደነበርም የፖለቲካ ተንታኞች ገለጸዋል።

መሳይ መኮንን

አበበ ፈለቀ

አርያም ተክሌ