1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሶማሊያ የባሕር ላይ ወንበዴዎችና ወታደራዊዉ ዘመቻ

ረቡዕ፣ ግንቦት 5 2001

የሶማሊያ የባሕር ላይ ወንበዴዎች በመርከቦች ላይ የሚያደርሱትን ጥቃትና እገታ ለመግታት የዘመተዉ አለም አቀፍ የባሕር ጦር እስካሁን የተፈለገዉን ያሕል ዉጤት አላመጣም።

https://p.dw.com/p/HpLk
የባሕር ላይ ወንበዴዎቹ እናት መረከብ
የባሕር ላይ ወንበዴዎቹ እናት መረከብምስል AP

ትናንት የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) የባሕር ሐይል አዛዥ ሆነዉ የተሾሙት አሜሪካዊዉ የባሕር ሐይል መኮንን አድሚራል ስታንበርግሰን የወንበዴዎቹን እንቅስቃሴ ለመግታት ጠንካራ እርምጃ ይወስዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።የባሕር ጉዞንና ዘረፋን የሚከታተለዉ ተቋም ኢንተርናሽናል ማሪታይም ቢሮ እንደሚለዉ ወታደራዊዉ ዘመቻ ጥቃትና እገታዉን ሙሉ በሙሉ አያስወግደዉም።የለንደኑ ወኪላችን ድልነሳ ጌታነሕ የቢሮዉን ሐላፊ አነጋግሮ የሚከተለዉን ዘገባ ልኮልናል።

ድልነሳ ጌታነሕ/ነጋሽ መሀመድ/አርያም ተክሌ