1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሶማሊያ አማፂ ቡድን መሪ ጉዞና የቡድኑ ማስተባበያ

ሐሙስ፣ መጋቢት 24 2001

አዌስ ከሶማሊያ መንግሥት ጋር ተስማሙ መባሉን ጃማዕ የአዉሮጳ ፕሮፓጋንዳ ብለዉታል

https://p.dw.com/p/HOeN
የሶማሊያ ደፈጣ ተዋጊዎጭምስል AP

ሕብረት ለሶማሊያ ዳግም ነፃነት (በእንግሊዝኛ ምሕፃሩ ARS) የተሰኘዉ አማፂ ቡድን መሪ ሼክ ሐሰን ዳሒር አዌስ ከሶማሊያ መንግሥት ጋር ሳይስማሙ አይቀሩም የሚለዉን ዘገባ መንበሩን አስመራ ያደረገዉ ቡድን አንድ ባለሥልጣን አስተባባሉ።ዩናይትድ ስቴትስና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በአሸባሪነት የፈረጇቸዉ ሼኽ ዳሒር አዌስ በካርቱም በኩል ወደ መቅዲሾ መጓዛቸዉን የዜና ወኪሎች ትናንት ዘግበዉ ነበር።የኤ አር ኤስ ሥራ-አስፈፃሚ ኮሚቴ ምክትል ሊቀመንበር ጃማዕ መሐመድ ዛሬ በተለይ ለዶቼ ቬለ እንደነገሩት ሼክ ዳሒር አዌስ ካርቱም መሔዳቸዉ እዉነት ነዉ።ከሶማሊያ መንግሥት ጋር ተስማሙ መባሉን ግን ጃማዕ የአዉሮጳ ፕሮፓጋንዳ ብለዉታል።ጎይቶም ቢሆን ከአስሥመራ።