የሶማሊያ ረሀብ መባባስ18 ሐምሌ 2003ሰኞ፣ ሐምሌ 18 2003በሶማሊያ የተከሰተው ረሀብ በየስድስት ደቂቃዎቹ ልዩነት የአንድ ሀጻን ህይወት እየተቀጠፈ ነው ሲል የጀርመን ዜና አገልግሎት ድርጅት DPA አተተ። በሶማሊያ የተከሰተውን ረሀብ ለመቃኘት የዶቼ ቬሌዋ ቤቲና ሩህል ሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ ተገኝታ የሚከተለውን ልካለች። ማንተጋፍቶት ስለሺ እንደሚከተለው አጠናቅሮታል።https://p.dw.com/p/Rc2aበረሐብ የተጎዳ አፍሪቃዊ ህፃንምስል dapdማስታወቂያየርስ በርስ ጦርነቱ ፍዳ አሳሯን ያበላት የሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ ውስጥ በፈራረሱት ህንፃዎች መካከል የሚገኝ አነስተኛ ቦታ ነው። እመንገዱ ዳር በሚገኙት ባለሶስት ጉልቻ ምድጃዎች ላይ የተጣዱት አራት ድስቶች ይንፈቀፈቃሉ። በቅርበት ደግም በመቶዎች የሚቆጠሩ ሶማሊያውያን አይኖች ከድስቶቹ ላይ ተክረዋል። ድስቶቹ ለዛሬ ለየት ባለ መልኩ ሩዝና የፍየል ስጋ እየበሰለባቸው ነው። ማንተጋፍቶት ስለሺ