የሶማሊያና የብሪታንያ ግንኙነት
ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 22 2005ማስታወቂያ
የብሪታንያዉ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ዊሊያም ሔግ በድብቅ ሞቃዲሾ ድረስ ሔደዉ የከፈቱት ኤምባሲ ባንዲራ ከማዉለብለብ በስተቀር ዲፕሎማቶች አልተመደቡበትም፥ሥራም አልጀመረም።በመጪዉ ሳምንት ለንደን ላይ በሚደረገዉ ጉባኤ ደግሞ ራሷን ነፃ መንግሥት አድርጋ የምትቆጥረዉ ሶማሊ-ላንድ እንደ ሐገር እንጂ እንደ ሶማሊያ ግማደ ግዛት እንደማትካፈል አስታዉቃለች።የብሪታንያን እርምጃና የሶማሊ ላንድ አቋም በተመለከተ ነጋሽ መሃመድ የለንደኑን ወኪላችንን ድልነሳ ጌታነሕን በስልክ አነጋግሮታል።
ድልነሳ ጌታነህ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ነጋሽ መሃመድ