1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የስፖርት ዘገባ

ማክሰኞ፣ መስከረም 2 2004

13ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በቅርቡ ደቡብ ኮሪያ ከተማ ዴጉ ላይ መካሄዱ ይታወሣል። ሻምፒዮናው በተለይ ለኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም በዓለምአቀፍ ውድድሮች የተለመደው አኩሪ ውጤት የተገኘበት አልነበረም።

https://p.dw.com/p/Rl7r
ምስል AP

የኢትዮጵያ አትሌቶች በአንዲት የወርቅ ሜዳሊያ ብቻ ተወስነው ሲቀሩ ኬንያውያኑ ተፎካካሪዎቻቸው በአንጻሩ ከመካከለኛ እስከ ረጅም ርቀት ሁሉን በመቆጣጠር ከዚህ ቀደም ያልታየ ታላቅ ስኬት ሊያገኙ በቅተዋል። በአንድ በኩል ኬንያ እጅግ ጠንካራ የሆኑ በርካታ ወጣት አትሌቶችን ማፍራቷ በሌላ በኩል ደግሞ ኢትዮጵያ ዓለም ላወቀና ላደነቃቸው ቀደምት ሯጮቿ ብቁ ተተኪ አለማግኘቷ በዴጉው ውድድር ላይ ኦልቶ የታየ ነገር ነው። እርግጥ ኢትዮጵያ ተሥፋ የሚጣልባቸው ወጣት አትሌቶችን ማፍራት ጨርሶ አቁማለች ማለት አይደለም። ይሁንና ግንባር ቀደምነትን በማስከበሩ ረገድ ጽናትና ቋሚነት እየጠፋ መሄዱ የሚያሳስብ ነገር መሆኑ አልቀረም። ችግሩ ምንድነው? መፍትሄውስ? የቀድሞውን ታዋቂ አሠልጣኝ ዶር/ወልደመስቀል ኮስትሬን በጉዳዩ አነጋግረናል።

መሥፍን መኮንን

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ