1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የስጋ ደዌ በሽታ

ማክሰኞ፣ ሰኔ 1 2002

በስጋ ደዌ በሽታ ግንዛቤ ዙሪያ መጽሃፍ ያሳተሙ ኢትዮዽያዊ

https://p.dw.com/p/NlRM
ምስል picture-alliance / dpa/dpaweb

አቶ ተክለሥላሴ ገላን ይባላሉ። መንግስታዊ ባልሆነ ድርጅት ውስጥ ይሰራሉ። በኢትዮዽያ በስጋ ደዌ በሽታ ላይ በህብረተሰቡ ውስጥ ስር የሰደደው የአመለካከት ችግር በቀላሉ ሊወገድ ባይችልም ለውጥ እንዳለ ይናገራሉ። አቶ ተክለስላሴ በስጋ ደዌ በሽታ ላይ ያተኮረ መጽሐፍ አሳትመዋል--የዛሬ 3 ዓመታት አከባቢ። መጽሐፉ ለዘመናት የቆየው የተዛቡ አመለካከቶችን ለማስወገድ የሚረዳ ነው። አቶ ተክለስላሴ ገላን በአካል ጉዳተኝነት ላይም ሰፊ ዘመቻ ያከናውናሉ። የስጋ ደዌ በሽታ ለአካል ጉዳት ከሚዳርጉ መንስዔዎች አንዱ በመሆኑ እንቅስቃሴአቸው ሁሉን ያጠቃለለ ነው።

መሳይ መኮንን

ነጋሽ መሐመድ