የስደተኞች መከራ በፈረንሣይ
ማክሰኞ፣ ሐምሌ 7 2007ማስታወቂያ
አብዛኛዎቹ ስደተኞች በሱዳን፣ በግብፅ እና በሊቢያ በረሃዎች መከራ የደረሰባቸው ናቸው። ከበረሃው ሀሩር አለያም ከአሸባሪዎች የሞት ጥላ ሸሽተው ፈረንሣይ የደረሱ እነዚህ ስደተኞች እዛው ፈረንሣይ ውስጥም ሌላ የሞት ጥላ እየተከተላቸው ነው። የዛሬው አውሮጳና ጀርመን ጥንቅር በፈረንሣይ የወደብ ከተማዋ ካሌ አድረገው ወደ ብሪታንያ ሲያቀኑ የሕይወት አደጋ ስለደረሰባቸው ኢትዮጵያውያን ይቃኛል። ኃይማኖት ጥሩነህ ስደተኞቹ አነስተኛ የላስቲክ ድንኳኖችን ጥለው ወደሰፈሩበት አካባቢ በማምራት የሚከተለውን ዘገባ አጠናቅራለች።
ሃይማኖት ጥሩነህ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አርያም ተክሌ