1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሴኔጋሉን ፕሬዝደንት በመቃወም ሰልፍ

እሑድ፣ የካቲት 11 2004

በምዕራብ አፍሪቃዊትዋ ሴኔጋል፣ የተቃዋሚው ወገን ደጋፊዎች የአገሪቱ ገዢ አብዱላሂ ዋዴ ለመጪው ሣምንት እሁድ በታቀደው የአገሪቱ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ላይ ሊሳተፉ አይገባም በሚል እንደገና የአደባባይ ሰልፍ አካሄዱ።

https://p.dw.com/p/145kA
የዳካሩ ብጥብጥምስል picture-alliance/dpa

በምዕራብ አፍሪቃዊትዋ ሴኔጋል፣ የተቃዋሚው ወገን ደጋፊዎች የአገሪቱ ገዢ አብዱላሂ ዋዴ ለመጪው ሣምንት እሁድ በታቀደው የአገሪቱ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ላይ ሊሳተፉ አይገባም በሚል እንደገና የአደባባይ ሰልፍ አካሄዱ።  ዋና ከተማይቱ ዳካር ውስጥ በተካሄደው ሰልፍ አኳያ በተቃዋሚዎችና በፖሊሶች መካከል ግጭት መድረሱም ተነግሯል። የፈረንሣይ ዜና አገልግሎት ወኪል ከስፍራው እንዳስታወቀው ፖሊስ ከአንድ የመስጊድ ጸሎት በኋላ ድንጋይ የወረወሩ ሰዎችን ለመበተን አስለቃሽ ጢስ ተጠቅሞ ነበር። የ 85 ዓመቱ አንጋፋ ዋዴ ምንም እንኳ ከሁለት የሥልጣን ዘመን በኋላ መወዳደር ባይችሉም ለሶሥተኛ ጊዜ በዕጩነት እንዲቀርቡ የፈቀደው የሴኔጋል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው። የሴኔጋል መንግስት ምንም አይንት ሰላማዊ ሰልፍን ቢያግድም፣ አምጹ ለአራተኛ ቀን ቀጥሎአል። ተቃዋሚዊች ፕሪዝድንት ዋዴ ስልጣን ላይ የሙጥኝ ያሉት ካሪም ለተሰኘዉ ልጃቸዉ ስልጣን ለማሸጋገር የወጠኑት ነዉ ሲሉ ይከሳሉ። በአገሪትዋ እንደሚገኝዉ የምርጫ ተመልካች ቡድን ግምት ዋዴ  አሸናፊ  ከሆኑ ፣ በሚቀጥለዉ  ሳምንት  እሁድ  በአገሪቱ  ከባድ  ረብሻ  ሊቀሰቀስ  ይችላል።  

አዜብ ታደሰ

መስፍን መኮንን

አዜብ  ታደሰ

መስፍን  መኮንን