1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሴት ልጅ ግርዛት ይቁም!

ማክሰኞ፣ የካቲት 2 2002

በዓለማችን በአንድ ቀን ዉስጥ 8,000 ታዳጊ ሴቶች ግርዛት ይፈጸምባቸዋል። በተመሳሳይ በየአስራ አንድ ሰከንዱ ደግሞ አንዷ ልጅ የዚህ ጎጂ ልማድ ሰለባ ትሆናለች።

https://p.dw.com/p/LxOK
ጎጂ ልማዱ የጠናባት የሶማሊያ ሴቶችምስል picture-alliance/ dpa

በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በሴት ልጆች ላይ የሚፈፀመዉን ይህን ጎጂ ባህላዊ ልማድ ለማስቆም የተጀመረዉ እንቅስቃሴ ፍሬ እያሳየ ቢሆንም ዛሬም ብዙ ሊሰራ እንደሚገባ እየተነገረ ነዉ። የሴትልጅ ግርዛት ይቁም የተሰኘዉን ዘመቻ ያዘከረዉ ዓመታዊ ዕለት ባሳለፍነዉ ሳምንት መጨረሻ ታስቧል። ዘመቻዉ በሴቶች ብቻ ሳይሆን የወንዶችንም ትብብር እንደሚሻ ነዉ የተነገረዉ።

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ