1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሳዑዲ ዓረቢያ/የውጡልኝ ቀነ ገደብ መራዘም እና የዜጎች ምሬት

ዓርብ፣ ሰኔ 23 2009

የሳዑዲ ዓረቢያ መንግስት ህገወጥ ባላቸው የውጭ ሀገር ዜጎች ላይ የጣለውን የዘጠና ቀን የውጡልኝ ቀነ ገደብ ለአንድ ወር ማራዘሙን አስታወቀ፡፡  በሪያድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከዛሬ ጀምሮ አዲስ የጉዞ ሰነድ መስጠትም ሆነ ተያያዥ ጉዳዮችን መመልከት ጀምሯል፡፡

https://p.dw.com/p/2fiF5
Saudi-Arabien Regierung verlängert Deadline für illegale Migranten aus Äthiopien um einen Monat
ምስል DW/S. Shibru

Ber. Riyadh(Saudi-Regierung verlängert Deadline_REAX Äthiopien) - MP3-Stereo

ከሳዑዲ ኣረቢያ የመውጣት ሀሳብ የሌላቸው ግን የቀነ ገደቡ መራዘም ትርጉም አልባ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡  የኢትዮጵያ አየር መንገድን ትኬት ይዘው ከነ ቤተሰቦቻቸው ለበርካታ ቀናት በኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አዳራሽ ተጥለው የሚገኙ መንገደኞች ደግሞ  የሰሚ ያለህ እያሉ ነው፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዛሬም ትኬት ለገዙት ኢትዮጵያዊያን ደንበኞቹ አንድም በውሉ መሰረት ሀገር አላደረሳቸው፤ ሁለትም የገዙበትን ትኬት ዋጋ አልመለሰላቸው እስከ ቀጣዩ በረራ ድረስ ሆቴል ሳያሳርፋቸው በኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አዳራሽ እየተንገላቱ ይገኛሉ፡፡  

ስለሺ ሽብሩ 


አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ