1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«የሲዳማ አንድነት ፓርቲ» ሲአን ዳግም ምርጫ እንዲካሄድ ጠየቀ

ማክሰኞ፣ ሰኔ 22 2013

ተቃዋሚው «የሲዳማ አንድነት ፓርቲ» ሲአን በሲዳማ ክልል የተካሄደው ምርጫ የተለያዩ ሕገ ወጥ ያላቸው ተግባራት የተፈጸሙበት ነው ሲል በክልሉ ዳግም ምርጫ እንዲካሄድ ጠየቀ። የፓርቲው ሃላፊዎች ትናንት አዲስ አበባ ውስጥ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በምርጫ እለት ደረሱብን ያሏቸውን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አቤት ማለታቸውን አስታውቀዋል።

https://p.dw.com/p/3vlb6
Süd Äthiopien Oppositionsparteien Wahlkampf
ምስል Shewangizaw Wegayehu/DW

Beri- AA (Sidama Unity Party demands for reelection ) - MP3-Stereo

ተቃዋሚው «የሲዳማ አንድነት ፓርቲ» ሲአን በሲዳማ ክልል የተካሄደው ምርጫ የተለያዩ ሕገ ወጥ ያላቸው ተግባራት የተፈጸሙበት ነው ሲል በክልሉ ዳግም ምርጫ እንዲካሄድ ጠየቀ።የፓርቲው ሃላፊዎች ትናንት አዲስ አበባ ውስጥ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫና ለዶቼቬለ በሰጡት ማብራሪያ በምርጫ እለት ደረሱብን ያሏቸውን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አቤት ማለታቸውን አስታውቀዋል። ፓርቲው ምርጫው በተካሄደበት እለት ደረሱብኝ ባላቸው ኢሕጋዊ ተግባራትም ከምርጫው ራሱን ማግለሉንም ይፋ አድርጓል።የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር  በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ተገኝቷል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር  
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ