1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሱዳን ድንበር ላይ ግጭት

ሐሙስ፣ የካቲት 21 2005

በሱዳን የድንበር ግዛት ብሉ ናይል ዉጊያ ተጠናክሮ መቀጠሉን ዘገባዎች ያመለክታሉ። ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ምንጮች ኤል ኩርሙክ የተሰኘችዉን ከተማ ለመያዝ ሰሞኑን በመንግስት ኃይሎችና በአማፅያን መካከል ጠንካራ ዉጊያ ካሄዱን ይገልፃሉ፤ የሱዳን ጦር በበኩሉ ዘገባዉን አስተባብሏል።

https://p.dw.com/p/17oLD

ዉጊያዉ በአካባቢዉ የሚገኙ ወገኖችን ማፈናቀል መቀጠሉም ተገልጿል። ኢትዮጵያ ዉስጥ ቀደም ሲል ድንበር አልፈዉ የገቡ ከ80 ሺህ በላይ የሱዳን ስደተኞች ይገኛሉ። በሰሞኑ ግጭት ምክንያት ግን አዲስ የመጣ ስደተኛ አለመኖሩን በኢትዮጵያ የተመ ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን አስታዉቋል። የፈረንሳይ የዜና ወኪል አዣንስ ፍራንስ ፕረስ እንደዘገበዉ ማንነታቸዉ እንዳይገለፅ የጠየቁ ምንጩ ካለፈዉ ሳምንት አንስቶ ስልታዊ በምትባለዉ የሱዳን የድንበር ግዛት ብሉናይል ጠንካራ ዉጊያ እየተካሄደ ነዉ። ወደዚህ ስፍራ ማለትም ወደብሉናይል እና ደቡብ ኮርዶፋን ደግሞ ምንም ዓይነት ገለልተኛ አካል እንዳይገባ የሱዳን መንግስት በጥብቅ ማገዱ ይነገራል። እንደዘገባዉም ባለፈዉ እሁድ ኤል ኩርሙክን ለመቆጣጠር የሱዳን ጦር ከአማፅያን ጋ እስከዛሬ ያልታየ የተባለዉን ከባድ ዉጊያ አካሂዷል።

Afrika Südsudan Südkordofan Flüchtlinge
ምስል Andreas Hansmann

በእዚህ አካባቢም የሱዳን ህዝብ ነጻ አዉጭ ንቅናቄ ሰሜን SPLM-N የተባለዉ አማፂ ቡድን ከጎርጎሮሳዊዉ 2011ዓ,ም አንስቶ ይፋለማል። በአካባቢዉ የሚካሄደዉ ዉጊያም ሲቪሉን ኅብረተሰብ ለከፋ አደጋ ባጋለጠ መልኩ አሳሳቢ መሆኑን የተመድ አመልክቷል። የመንግስታቱ ድርጅት እንደሚለዉም በግጭቱ ምክንያትም እስካሁን ከሁለት መቶ ሺህ የሚበልጡ ወገኖች ወደደቡብ ሱዳንን ኢትዮጵያ ተሰደዋል። ተጨማሪ አንድ ሚሊዮን የሚሆን ህዝብም በብሉናይል እና ደቡብ ኮርዶፋን ለችግር መዳረጉን የአማፂዉ ቡድን የሰብዓዊ ጉዳዮች ዘርፍና የመንግስት የረድኤት ድርጅቶች ያመለክታሉ። የሰሞኑ ወጊያም ተጨማሪ ሰዎች ከቤት ንብረታቸዉ እንዲፈላቀሉ አስገድዷል፤ ኩርሙክ ከተማ አልቦ ሰዉ ቀርታለች። የአማፅያኑ ቃል አቀባይ አርኑ ናጉቱሉ ሎዲ እንደሚሉትም አብዛኞቹ የከተማዋ ኗሪዎች ተሰደዋል። አብዛኞቹ ስደተኞች ወደጎረቤት ሀገሮች ማለትም ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን መግባታቸዉ ቢገለፅም በአሁኑ ወቅት አዲስ ስደተኞች ድንበር እንዳልተሻገሩ ነዉ የተመ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ከኢትዮጵያ ያመለከተዉ።

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ