1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሱዳን ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤትና የተቃዋሚዎች ስምምነት

ሐሙስ፣ ሐምሌ 11 2011

የሱዳን ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤትና የስቪል አስተዳደር እንዲመሰረት ሲወተዉቱ የነበሩት የተቃዋሚ ሀይሎች በዛሬው ዕለት ስልጣን ለመጋራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራርመዋል።

https://p.dw.com/p/3MDXV
Sudan Khartoum | Mohamed Hamdan Dagalo und Protestführer unterschreiben Abkommen
ምስል Getty Images/AFP/H. El-Tabei

የሱዳን ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤትና የተቃዋሚዎች ስምምነት

የሱዳን ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤትን የስቪል አስተዳደር እንዲመሰረት ሲወተዉቱ የነበሩት የተቃዋሚ ሀይሎች በዛሬው ዕለት ስልጣን ለመጋራት የሚያስችላቸዉን ስምምነት ተፈራርመዋል።
ሁለቱ የሱዳን የፓለቲካ ሀይሎች በዛሬዉ ዕለት ስምምነት ላይ የደረሱት በኢትዮጵያና በአፍሪካ ህብረት ቀርቦ ስምምነት ላይ ደርሰዉበት በነበረዉ ረቂቅ የሽግግር እቅድ መሆኑን የኢትዮጵያ የዉጭ ጉዳይ ሚንስቴር ባወጣዉ መግለጫ ገልጿል።  
እንደ ኢትዮጵያ ዉጭ ጉዳይ ሚንስትር መግለጫ በሱዳን የተፈረመዉ የፖለቲካ ስምምነት የመንግስት አወቃቀርንና በሽግግሩ ወቅት ትኩረት የሚሰጣቸዉን ጉዳዮች የሚገዛ ሰነድ ነዉ።
የአፍሪካ ኅብረት ዋና አደራዳሪ መሐመድ ኢል ሐሲን ሌባት ስምምነቱ ሁለቱን ወገኖች ወደ አጠቃላይ ዕርቅ የሚመራና ነዉ ብለዉታል።
የሰነዱ መፈረም በብዙዎች ዘንድ ወታደሩ የቀድሞውን የሱዳን ፕሬዝዳንት ኦማር ኧል-በሽርን ባለፈው ሚያዚያ ከሥልጣን ካስወገደ ወዲህ የተወሰደ ትልቅ እርምጃ ነዉ ተብሏል።በሱዳን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ልዩ መልዕክተኛ እና አደራዳሪ አምባሳደር መሐሙድ ድሪርም ከስምምነቱ በኋላ ባደረጉት ንግግር የሱዳን ህዝብ ለዚህ ታሪካዊ ወቅት መድረሱ ታላቅ ነገር ነው ብለዋል።    
«የሱዳን ህዝብ ለዚህ  ታሪካዊ  ወቅት  መድረሱ ታላቅ  ነገር  ነው። የተለያዩ የሱዳን አካላት ማለት አልፈልግም ከዚያ ይልቅ አንድ አካል የጀግናውን የሱዳን ጦር፣የሽግግር ምክር ቤቱን፣ለዴሞክራሲ በመቆም አደባባይ የወጣውን አብዮታዊውን ወጣት፣ለዲሞክራሲ ሲሉ አደባባይ የወጡ  ምሁራንን  እና ፋናወጊዎችን የሚወክል የተባበረ ግንባር ነው የምለው።»   
የሱዳን ወታደራዊ ምክር ቤት ምክትል ሊቀመንበር መሀመድ ሃምዳን ዶጋሊ ከስምምነቱ በኋላ ባደረጉት ንግግር ደግሞ ስምምነቱን ለሀገሪቱ ታሪካዊ ክስተት ነው ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
«ዛሬ ጠዋት ለህዝባችን መልካም ምኞቴን ስገልጽ በጣም ደስ እያለኝ ነው።ወታደራዊው ምክር ቤት እና የነጻነት እና የለውጥ አራማጅ ኃይሎች የመጀመሪያውን ሰነድ መፈራረማቸው በሱዳን ህዝቦች ህይወት ውስጥ እንደ አንድ ታሪካዊ ወቅት የሚቆጠር ነው።»
በሱዳን ለተጀመረዉን የለዉጥ ሂደት ጉልህ ሚና ይኖረዋል የተባለውን የሥልጣን መጋራት ስምምነት በተቃዋሚዎች ዘንድም አድናቆት እየተቸረዉ ነዉ።ይህንን ተከትሎ የነፃነትና የለዉጥ ሀይል የተባለዉ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ኢብራሂም አል አሚን ለስምምነቱ ያላቸዉን አድናቆት ገልፀዉ፤ባለፉት የተቃዉሞ ወራት በፀጥታ ሀይሎች ህይወታቸዉን ያጡ፤ በሁሉም ሱዳናዉያን ዘንድ ከበሬታ አላቸዉ ብለዋል።
"በመላ ሱዳን በደቡብ,፣በሰሜን እና በምዕራብ  ይህንን ታሪካዊ  ቀን በማክበር  ላይ የሚገኝ ሁሉ ለሱዳን ሲሉ ሕይወታቸውን መሥዋዕት ላደረጉ ሰማዕታት ክብር  አለዉ።»
በስምምነቱ መሰረት 11 አባላት የሚኖሩት የሉዓላዊ ምክር ቤት ይቋቋማማል። አምስቱ የምክር ቤት አባላት ከጦሩ አምስቱ አባላት ደግሞ ከሲቪል የሚመረጡ ሲሆን ቀሪዉ አንድ አባል ከገለልተኛ ወገን ይሆናል።ይህ ምክር ቤት በሱዳን ምርጫ እስኪከናወን ድረስ ለሦስት አመት ከሶስት ወር የሚያስተዳድር ሲሆን ለመጀመሪያዎቹ 21 ወራት የጦሩ ተወካዮች ፤ ለሚቀጥሉት 18 ወራት ደግሞ ከስቢል ተወካዮች ሀገሪቱን የሚመሩ ይሆናል።
ለ ሶስት አስርተ ዓመታት ሱዳንንን የመሩት ኦማር ሐሰን አል በሽር ከሥልጣን ከተወገዱ ካለፈዉ ሚያዚያ ወዲህ በሀገሪቱ የተፈፀሙ የህግ ጥሰቶች በገለልተኛ ኮሚሽን እንዲጣራ ሁለቱ ወገኖች ስምምነት ላይ ደርሰዋል። ያም ሆኖ ግን ሁለቱ ወገኖች አወዛጋቢ በሆነው በሥገ-መንግሥታዊ የሥራ ክፍፍል ላይ የጀመሩትን ድርድር በይደር አቆይተዉታል።

Sudan | Demonstration in Khartoum
ምስል Getty Images/AFP/A. Shazly
Sudan Khartoum | Friedensgespräche
ምስል picture-alliance/AA/M. Hjaj

 ፀሐይ ጫኔ

አዜብ ታደሰ