1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሱዳን ብሉ ናይል ስደተኞች ቁጥር መጨመር

ረቡዕ፣ ጥቅምት 15 2004

በሱዳኗ የብሉ ናይል ግዛት በተባባሰው ውጊያ ምክንያት ከአካባቢው የሚሰደዱት ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መሄዱን የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን በእንግሊዘኛው ምህፃር UNHCR አስታወቀ ።

https://p.dw.com/p/Rt9u
ምስል picture-alliance/ dpa

UNHCR እንደተናገረው በግዛቲቱ ውጊያ ከተቀሰቀሰበት ካላፈው ወር አንስቶ ከብሉ ናይል ተፈናቅለው ወደ ኢትዮጵያ የገቡት ስደተኞች ቁጥር ከ 28 ሺህ በልጧል ። ድርጅቱ እንደሚለው ውጊያው ከቀጠለ በመጪዎቹ ሳምንታት ወደ ጎረቤት አገራት የሚሰደዱት ቁጥር ከፍ ማለቱ አይቀርም ። ስለ ብሉ ናይል ስደተኞች ሁኔታ ሂሩት መለሰ በኢትዮጵያ የ UNHCR የህዝብ መረጃ ክፍል ሃላፊ አቶ ክሱት ገብረ እግዚአብሔርን አነጋግራ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅራለች ።

ሂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ