የሱዳንና ደቡብ ሱዳን ያለመጠቃቃት ውል
ሰኞ፣ የካቲት 5 2004ማስታወቂያ
ሱዳንና ደቡብ ሱዳን በአፍሪቃ ሕብረት አማካይነት አዲስ አበባ ላይ ባካሄዱት ድርድር እርስበርስ ያለመጠቃቃት ውል ተፈራረሙ። ውሉን የተፈራረሙት የሱዳን የጸጥታ ሃላፊ ሞሐመድ አታና የደቡብ ሱዳኑ አቻቸው ቶማስ ዱዝ ሲሆኑ ውሉን ያፈራረሙት ዋነኛው አደራዳሪ የቀድሞው የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዚደንት ታቦ እምቤኪ ናቸው። በስምምነቱ ሁለቱ ወገኖች አንዱ የሌላውን ወገን ሉዓላዊነትና ግዛታዊ ነጻነት ለማክበር፤ እንዲሁም ከማንኛውም ጥቃት ለመቆጠብ ቃል ገብተዋል። ዝርዝሩን የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ጌታችዉ ተድላ ሃይለጊዮርጊስ ልኮልናል
ጌታችዉ ተድላ ሃ/ጊዮርጊስ
አዜብ ታደሰ
ሂሩት መለስ