1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሰቆጣ ቃል-ኪዳንና ተጨባጭ ለዉጥ ለማምጣት የሚደረግ እንቅስቃሴ

ዓርብ፣ መጋቢት 6 2011

በአማራ ክልል ሰቆጣና አዋሳኝ የትግራይ ክልል ወረዳዎች የሚታየዉ የህፃናት መቀንጨርና ሌሎች ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል ተባለ። ከተወሰኑ ዓመታት በፊት ችግሮችን ለመፍታት የተፈረመው የሰቆጣ ቃል-ኪዳን የተሰኘ ስምምነት የእስካሁን አፈፃፀም ሂደትን ለመታዘብ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሐላፊዎች ጉብኝት አሰድርገዋል።

https://p.dw.com/p/3F8jT
Amhara Polizeikommissar  Zelalem Lijalem und Polizeistation
ምስል DW/A. Mekonnen

በአማራ ክልል ሰቆጣና አዋሳኝ የትግራይ ክልል ወረዳዎች ያለው ከፍተኛ መጠን ያለው የህፃናት መቀንጨር እንዲሁም ሌሎች ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል ተባለ። ከተወሰኑ ዓመታት በፊት የአዋሳኝ አካባቢው ዘርፈ ብዙ ችግሮች ለመፍታት የተፈረመው የሰቆጣ ቃል-ኪዳን የተሰኘ ስምምነት የእስካሁን አፈፃፀም ሂደት ለመታዘብ የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት ከፍተኛ የስራ ሐላፊዎች በአካባቢው ጉብኝት ሲያደርጉ ሰንብተዋል። በአማራ ክልል ሰቆጣ እንዲሁም በአዋሳኝ የትግራይ ክልል ወረዳዎች አሁንም የድህነት መጠኑ ከፍተኛ መሆኑ፣ ለህፃናት የተመቻቸ ሁኔታ እንደሌለ በጉብኝታቸው ወቅት እንደታዘቡ የፌደራል መንግስት ሚኒስቴሮች ገልፀዋል። የሰቆጣ ቃል-ኪዳን እንደሚያመለክተው እስከ 2020 የኢትዮጵያውያን አቆጣጠር በአካባቢው ተጨባጭ ለውጥ  ለማምጣት ታቅዷል። ከዚህም አንዱ የህፃናት መቀንጨር መጠን አሁን ካለው 54 በመቶ ወደ ዜሮ ማውረድ ይገኝበታል።

ሚሊዮን ኃይለሥላሴ 
አዜብ ታደሰ 
እሸቴ በቀለ